YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 43

43
1አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ። 2በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም። 3እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም#ዕብ. “ሳባን” ይላል። ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ። 4በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ። 5እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ ዘር​ህ​ንም ከም​ሥ​ራቅ አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ከም​ዕ​ራ​ብም እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ። 6ሰሜ​ንን፦ መል​ሰህ አምጣ፤ ደቡ​ብ​ምን፦ አት​ከ​ል​ክል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችን ከሩቅ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ከም​ድር ዳርቻ፥ 7በስሜ የተ​ጠ​ራ​ውን ለክ​ብ​ሬም የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን፥ የሠ​ራ​ሁ​ት​ንና ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ አምጣ” እለ​ዋ​ለሁ።
8ዐይ​ኖች እያ​ሉ​አ​ቸው የማ​ያዩ ዕው​ሮ​ችን ሕዝብ፥ ጆሮ​ችም እያ​ሉ​አ​ቸው የማ​ይ​ሰሙ ደን​ቆ​ሮ​ዎ​ችን አወ​ጣሁ። 9አሕ​ዛብ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ፤ አለ​ቆ​ችም ተከ​ማቹ፤ ይህን ማን ይና​ገ​ራል? የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል? ይጸ​ድቁ ዘንድ ምስ​ክ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ያምጡ፤ ሰም​ተ​ውም፦ እው​ነ​ትን ይና​ገሩ። 10ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም። 11እኔ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ የሚ​ያ​ድን አም​ላክ የለም። 12ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አድ​ኜ​ማ​ለሁ፤ መክ​ሬ​ማ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ባዕድ አም​ልኮ አል​ነ​በ​ረም፤ ስለ​ዚህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ፤ 13ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?
14የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ የሚ​ቤ​ዣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ እና​ንተ ወደ ባቢ​ሎን ሰድ​ጃ​ለሁ፤ ስደ​ተ​ኞ​ችን አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በመ​ር​ከብ ውስጥ ይታ​ሰ​ራሉ። 15ቅዱ​ሳ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ፈጣሪ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እኔ ነኝ።” 16በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦ 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና ፈረ​ሱን ሠራ​ዊ​ቱ​ንና አር​በ​ኛ​ውን ያወ​ጣል፤ እነ​ርሱ ግን በአ​ን​ድ​ነት ተኝ​ተ​ዋል፤ አይ​ነ​ሡም፤ ቀር​ተ​ዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስ​ታ​ሪም ጠፍ​ተ​ዋል፤ 18የፊ​ተ​ኛ​ውን ነገር አታ​ስ​ታ​ውሱ፤ የጥ​ን​ቱ​ንም ነገር አታ​ስቡ። 19እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 20የም​ድረ በዳ አራ​ዊት፥ ቀበ​ሮ​ችና ሰጎ​ኖች፥ ያከ​ብ​ሩ​ኛል። የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ሕዝ​ቤን አጠጣ ዘንድ በም​ድረ በዳ ውኃን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን ሰጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ 21እነ​ር​ሱም ምስ​ጋ​ና​ዬን እን​ዲ​ና​ገሩ ለእኔ የፈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ሕዝብ ናቸው፤
22ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እነሆ፥ አል​ጠ​ራ​ሁ​ህም፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አል​ዘ​በ​ዘ​ብ​ሁ​ህም፤ 23ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በጎ​ች​ህን አላ​ቀ​ረ​ብ​ህ​ል​ኝም፤ በሌ​ላም በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትህ አላ​ከ​በ​ር​ኸ​ኝም፤ በእ​ህ​ልም ቍር​ባን አላ​ስ​ቸ​ገ​ር​ሁ​ህም፤ በዕ​ጣ​ንም አላ​ደ​ከ​ም​ሁ​ህም። 24ዕጣ​ንም በገ​ን​ዘብ አል​ገ​ዛ​ህ​ል​ኝም፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህ​ንም ስብ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን በኀ​ጢ​አ​ት​ህና በበ​ደ​ልህ በፊቴ ቁመ​ሃል።
25መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም። 26አሳ​ስ​በኝ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆነን እን​ፋ​ረድ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ድቅ አስ​ቀ​ድ​መህ በደ​ል​ህን ተና​ገር። 27በመ​ጀ​መ​ሪያ አባ​ቶ​ችህ፥ ቀጥ​ሎም አለ​ቆ​ችህ በድ​ለ​ው​ኛል። 28አለ​ቆች መቅ​ደ​ሴን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚ​ህም ያዕ​ቆ​ብን ለጥ​ፋት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለው​ር​ደት ሰጠሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 43