YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 44

44
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ
1አሁ​ንም ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ። 2የፈ​ጠ​ረህ ከማ​ኅ​ፀ​ንም የሠ​ራህ የሚ​ረ​ዳ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፥ “ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም ወዳጄ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ፍራ። 3በደ​ረቅ መሬት ላይ ለሚ​ሄ​ድና ለተ​ጠማ ውኃን እሰ​ጣ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴን በዘ​ርህ ላይ፥ በረ​ከ​ቴ​ንም በል​ጆ​ችህ ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ 4በውኃ መካ​ከል እን​ዳለ ቄጠማ በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጠ​ገብ እን​ደ​ሚ​በ​ቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች ይበ​ቅ​ላሉ። 5ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”
6የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም። 7እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነ​ሣና ይጥራ፤ ይና​ገ​ርም፤ ሰውን ከፈ​ጠ​ር​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሳይ​ደ​ርስ ይና​ገር። 8ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”
ስለ ጣዖት አም​ልኮ ከን​ቱ​ነት
9ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ቀ​ርጹ ያን​ጊዜ አይ​ኖ​ሩም፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል የሚ​ሠ​ሩም ሁሉ ከን​ቱ​ዎች ናቸው፤ የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን የራ​ሳ​ቸ​ውን ፍላ​ጎት የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ያፍ​ራሉ። 10ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ውን ምስል የሚ​ቀ​ር​ጹና በእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠሩ ሁሉ ይደ​ር​ቃሉ። 11ከሰ​ዎች መካ​ከል ደን​ቆ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቁሙ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም።
12ብረት ሠሪ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ውን ይስ​ላል፤ ጣዖ​ቱን በመ​ጥ​ረ​ቢያ ይቀ​ር​ጸ​ዋል፤ በመ​ዶ​ሻም መትቶ ቅርጽ ይሰ​ጠ​ዋል፤ በክ​ን​ዱም ኀይል ይሠ​ራ​ዋል፤ እር​ሱም ይራ​ባል፤ ይደ​ክ​ም​ማል፤ ውኃም አይ​ጠ​ጣም። 13ጠራ​ቢ​ውም እን​ጨት ቈርጦ በልኩ ያቆ​መ​ዋል፤ በማ​ጣ​በ​ቂ​ያም ያያ​ይ​ዘ​ዋል፤ በሰው አም​ሳ​ልና በሰው ውበት ያስ​መ​ስ​ለ​ዋል፤ በቤ​ትም ውስጥ ያቆ​መ​ዋል። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ቀ​ለ​ውን፥ በዝ​ና​ምም ያሳ​ደ​ገ​ውን ዛፍ ከዱር ይቈ​ር​ጣል። 15ለሰ​ውም ማገዶ ይሆ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ወስዶ ይሞ​ቃል፤ አን​ድ​ዶም እን​ጀራ ይጋ​ግ​ር​በ​ታል፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን ጣዖ​ታ​ትን አበ​ጅቶ ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።#ዕብ​ራ​ይ​ስጥ ይጨ​ም​ራል። 16ግማ​ሹን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል፤ በዚ​ያም በግ​ማሹ ሥጋ ይጠ​ብ​ሳል፤ ጥብ​ሱ​ንም ይበ​ላና ይጠ​ግ​ባል፤ ይሞ​ቃ​ልና፥ “እሰይ ሞቅሁ፥ እሳ​ቱን አይ​ቻ​ለሁ” ይላል። 17የቀ​ረ​ው​ንም እን​ጨት ጣዖት አድ​ርጎ ምስል ይቀ​ር​ጽ​በ​ታል፤ በፊ​ቱም ተጐ​ን​ብሶ ይሰ​ግ​ዳል፤ ወደ እር​ሱም እየ​ጸ​ለየ፥ “አም​ላኬ ነህና አድ​ነኝ” ይላል።
18አያ​ው​ቁም፤ አያ​ስ​ቡም፤ እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልቦ​ቻ​ቸው ተጋ​ር​ደ​ዋል። 19ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም። 20እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዳ​ኝ​ነት
21ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል፥ አገ​ል​ጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ባሪ​ያዬ ነህ፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ር​ሳኝ። 22መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።
24ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ 25በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት#ግእዝ “ምክር” ይላል። የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል። 26የባ​ር​ያ​ውን ቃል ያጸ​ናል፤ የመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ምክር ይፈ​ጽ​ማል። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም” ይላል። ከተ​ሞች ትታ​ነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ምድረ በዳ​ዎ​ች​ዋም ይለ​መ​ል​ማሉ፤” ይላል፤ 27ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤ 28ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in