YouVersion Logo
Search Icon

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 21

21
ለሐ​ዋ​ር​ያት በጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ባሕር ስለ መገ​ለጡ
1ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ባሕር አጠ​ገብ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ደ​ገና ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው። 2ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማስ፥ ከገ​ሊላ ቃና የሆ​ነው ናት​ና​ኤል፥ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆ​ችና ሌሎ​ችም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለት አብ​ረው ነበሩ። 3#ሉቃ. 5፥5። ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ “እኔ ዓሣ ላጠ​ምድ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛም አብ​ረ​ንህ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት፤ ሄደ​ውም ወደ ታንኳ ገቡ፤ ግን በዚ​ያች ሌሊት የያ​ዙት ምንም የለም።
4በነጋ ጊዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በባ​ሕሩ ዳር ቆሞ ነበር፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አዩት፤ ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ አላ​ወ​ቁም። 5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ልጆች ሆይ አን​ዳች የሚ​በላ ነገር አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት። 6#ሉቃ. 5፥6። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መረ​ባ​ች​ሁን በታ​ን​ኳ​ዪቱ በስ​ተ​ቀኝ በኩል ጣሉ፤ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው፤#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “መላ ሌሊ​ቱን ደከ​ምን፤ ምንም ያያ​ዝ​ነው ነገር የለም፤ ነገር ግን በአ​ንተ ቃል እን​ጥ​ላ​ለን አሉት” የሚ​ለ​ውን ከሉ​ቃስ ምዕ. 5 ቍ. 15 ያለ​ውን አም​ጥቶ ይጽ​ፋል። መረ​ባ​ቸ​ው​ንም በጣሉ ጊዜ ከተ​ያ​ዘው ዓሣ ብዛት የተ​ነሣ ስቦ ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው። 7ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በረ ያ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ለጴ​ጥ​ሮስ፥ “ጌታ​ችን ነው እኮ” አለው፤ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ጌታ​ችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚ​ለ​ብ​ሰ​ውን ልብስ አን​ሥቶ በወ​ገቡ ታጠቀ፤ ራቁ​ቱን ነበ​ርና ወደ ባሕር ተወ​ረ​ወረ። 8ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን በታ​ንኳ መጡ፤ ከሁ​ለት መቶ ክንድ ያህል በቀር ከም​ድር አል​ራ​ቁም ነበ​ርና፤ ዓሣ የመ​ላ​ባ​ቸ​ውን መረ​ቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም እየ​ሳቡ ሄዱ።
9ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ፍሙ መርቶ፥ ዓሣም በላዩ ሆኖ፥ እን​ጀ​ራም ተሠ​ርቶ አገኙ። 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አሁን ከያ​ዛ​ች​ኋ​ቸው ዓሣ​ዎች አምጡ” አላ​ቸው። 11ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ታንኳ ገብቶ መቶ አምሳ ሦስት ታላ​ላቅ ዓሣ​ዎ​ችን መልቶ የነ​በ​ረ​ውን መረብ ወደ ምድር ሳበ፤ ብዛ​ቱም ይህን ያህል ሲሆን መረቡ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም። 12ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ኑ፥ ምሳ ብሉ” አላ​ቸው፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አንተ ማነህ? ብሎ ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ የለም፤ ጌታ​ችን እንደ ሆነ ዐው​ቀ​ዋ​ልና። 13ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጣና ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሲገ​ለ​ጥ​ላ​ቸው ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜዉ ነበር።
ጌታ​ችን ጴጥ​ሮ​ስን ትወ​ደ​ኛ​ለህ ወይ ብሎ እንደ ጠየ​ቀው
15ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው። 16ዳግ​መ​ኛም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “ጠቦ​ቶ​ችን አሰ​ማራ” አለው። 17ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው። 18“እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ አንተ ጐል​ማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ወደ ወደ​ድ​ኸው ትሄድ ነበር፤ በሸ​መ​ገ​ልህ ጊዜ ግን እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ሌላ ያስ​ታ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ወደ​ማ​ት​ወ​ደ​ውም ይወ​ስ​ድ​ሃል።” 19በምን ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያከ​ብር ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት ይህን ተና​ገረ፤ ይህ​ንም ብሎ ተከ​ተ​ለኝ አለው።
ስለ ወን​ጌ​ላ​ዊው ዮሐ​ንስ
20ጴጥ​ሮ​ስም መለስ ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በ​ረ​ውን ያን ደቀ መዝ​ሙር ሲከ​ተ​ለው አየ፤ እር​ሱም ራት ሲበሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውና “ጌታ ሆይ፥ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥህ ማነው?” ያለው ነው። 21ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን አይቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ ይህስ እን​ዴት ይሆ​ናል?” አለው። 22ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው። 23ያም ደቀ መዝ​ሙር እን​ደ​ማ​ይ​ሞት ይህ ነገር በወ​ን​ድ​ሞች ዘንድ ተነ​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን፥ “እስ​ክ​መጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ” አለ እንጂ አይ​ሞ​ትም አላ​ለ​ውም።
24ስለ​ዚህ ነገር ምስ​ክር የሆነ፥ ስለ እር​ሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝ​ሙር ነው፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን።
25ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሠ​ራ​ቸው ሌሎች ብዙ ሥራ​ዎች አሉ፤ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ቢጻፍ ግን የተ​ጻ​ፉ​ትን መጻ​ሕ​ፍት ዓለም ስን​ኳን ባል​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበር።
ከዐ​ሥራ ሁለቱ ሐዋ​ር​ያት አንዱ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጅ ሐዋ​ር​ያው ዮሐ​ንስ ጌታ​ችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠ​ላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነ​ገሠ በሰ​ባት ዓመት በዮ​ና​ና​ው​ያን ቋንቋ ለኤ​ፌ​ሶን ሰዎች የጻ​ፈ​ፍው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in