የዮሐንስ ወንጌል 9
9
ዕዉር ሆኖ የተወለደውን ስለ ማዳኑ
1ከዚያም ሲያልፍ ዕዉር ሆኖ የተወለደውን ሰው አየ። 2ደቀ መዛሙርቱም፥ “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኀጢኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት። 3ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔር ሥራ ሊገለጥበት ነው እንጂ እርሱ አልበደለም፤ ወላጆቹም አልበደሉም። 4ነገር ግን ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ልሠራ ይገባኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና። 5#ማቴ. 5፥14፤ ዮሐ. 8፥12። በዓለም ሳለሁ፤ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።” 6ይህንም ብሎ በምድር ላይ ምራቁን እንትፍ አለ፤ በምራቁም ጭቃ አድርጎ የዕዉሩን ዐይኖች ቀባው። 7እንዲህም አለው፥ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” ትርጓሜውም የተላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠበና እያየ ተመለሰ። 8ጎረቤቶቹና ቀድሞ የሚያውቁት፥#“የሚያውቁት” የሚለው በግሪኩ የለም። ሲለምንም ያዩት የነበሩት ግን፥ “ይህ በመንገድ#“በመንገድ” የሚለው በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ የለም። ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለም?” አሉ። 9“ይህ እርሱ ነው” ያሉ አሉ፤ ሌሎችም፥ “አይደለም፤ ይመስለዋል እንጂ” አሉ፤ እርሱ ራሱ ግን፥ “እኔ ነኝ” አለ። 10እነርሱም፥ “ዐይኖችህ እንዴት ተገለጡ?” አሉት። 11እርሱም መልሶ፥ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው በምራቁ ጭቃ አድርጎ ዐይኖችን ቀባኝና ሂደህ በሰሊሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠብሁና አየሁ” አላቸው። 12አይሁድም፥ “ሰውየው የት አለ?” አሉት፤ እርሱም፥ “አላውቅም” አላቸው።
13ያን ዕዉር ሆኖ የተወለደውንም ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። 14ጌታችን ኢየሱስ በምራቁ ጭቃ አድርጎ ዐይኖቹን ያበራበት ቀኑ ሰንበት ነበርና። 15ፈሪሳውያንም እንዴት እንዳየ ዳግመኛ ጠየቁት፤ እርሱም፥ “በምራቁ ጭቃ አድርጎ በዐይኖች አኖረው፥ ታጥቤም አየሁ” አላቸው። 16ከፈሪሳውያንም አንዳንዶች፥ “ይህ ሰው ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ሰንበትን አያከብርምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢኣተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ እንዴት ይችላል?” አሉ፤ እርስ በርሳቸውም ተለያዩ። 17ዳግመኛም ዕዉሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ዐይኖችህን ከፍቶልሃልና” አሉት፤ እርሱም፥ “ነቢይ ነው” አላቸው።
18አይሁድም የዚያን ያየውን ሰው ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወለደ፥#ግሪኩ “ዕዉር እንደ ነበረ” ይላል። እንዳየም አላመኑም። 19“ዕዉር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? እንግዲያ አሁን እንዴት ያያል?” ብለው ጠየቁአቸው። 20ወላጆቹም መልሰው እንዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወለደ እናውቃለን። 21አሁን ግን እንዴት እንደሚያይ ዐይኖቹንም ማን እንደ አበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መናገር ይችላልና።” 22ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ በእርሱ የሚያምን ቢኖር ከምኵራብ ይውጣ” ብለው አይሁድ ተስማምተው ነበርና። 23ስለዚህም ወላጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እርሱን ጠይቁት” አሉ። 24ዕውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፥ “ሂድ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ፤ ይህ ሰው ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን” አሉት። 25ያም ሰው መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እርሱ ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኔ አላውቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ።” 26ዳግመኛም፥ “ምን አደረገልህ? ዐይኖችህንስ እንደምን አበራልህ?” አሉት። 27እርሱም መልሶ፥ “አትሰሙኝም እንጂ ነገርኋችሁ፤ እንግዲህ ደግሞ ምን ልትሰሙ ትሻላችሁ? እናንተም ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁን?” አላቸው። 28እነርሱም ሰደቡት፤ እንዲህም አሉት፥ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን። 29እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተነጋገረው እናውቃለን፤ ይህን ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም።” 30ያም ሰው መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከወዴት እንደ ሆነ፥ አታውቁትምና ይህ እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዐይኖችን አበራልኝ። 31እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን። 32ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ዕዉር ሆኖ የተወለደውን ዐይኖች ያበራ አልተሰማም። 33ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ምንም ማድረግ ባልቻለም ነበር።” 34እነርሱም መልሰው፥ “ራስህ በኀጢኣት የተወለድህ አንተ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወጡት። 35ጌታችን ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ፤ አገኘውምና፥ “አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን?” አለው። 36ያ ሰውም፥ “አቤቱ፥ አምንበት ዘንድ እርሱ ማነው?” ብሎ መለሰለት። 37ጌታችን ኢየሱስም፥ “የምታየው፥ ከአንተ ጋርም የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው። 38እርሱም፥ “አቤቱ፥ አምናለሁ” ብሎ ሰገደለት። 39ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ የማያዩት እንዲያዩ፥ የሚያዩትም እንዲታወሩ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጥቻለሁ” አለው። 40ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሲናገር ሰምተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉሮች ነን?” አሉት። 41ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዕዉሮችስ ብትሆኑ ኀጢኣት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን እናያለን ትላላችሁ፤ አታዩምም፤ ስለዚህም ኀጢኣታችሁ ጸንቶ ይኖራል” አላቸው።
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 9: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: