YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 41

41
1አት​ፈ​ራ​ምን? ለእኔ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ሃ​ልና።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
የሚ​ቃ​ወ​መ​ኝስ ማን ነው?
2የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝና በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ርስ ማን ነው?
ከሰ​ማይ በታች ያለ​ውም ሁሉ የእኔ ነው።
3ስለ እርሱ ዝም አል​ልም፥
የኀ​ይል ቃልም እንደ እርሱ ያለ​ውን ይቅር ይለ​ዋል።
4የፊ​ቱን መጋ​ረጃ ማን ይገ​ል​ጣል?#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
ወደ ደረቱ መጋ​ጠ​ሚያ ውስ​ጥስ ማን ይገ​ባል?
5የፊ​ቱ​ንስ ደጆች የሚ​ከ​ፍት ማን ነው?
በጥ​ር​ሶቹ ዙሪ​ያም ግርማ አለ።
6አን​ጀ​ቶቹ የናስ አራ​ዊት ናቸው፤
የቆ​ዳ​ውም ጽናት እንደ ዓለት ድን​ጋይ ነው።
7እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጣ​በቁ ናቸ​ውና፥
ነፋ​ስም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው መግ​ባት አይ​ች​ልም።
8ሰውን ከወ​ን​ድሙ ጋር አንድ ያደ​ር​ጋል፤
እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ገ​ጣ​ጠሙ ናቸው፤ ሊለ​ያ​ዩም አይ​ች​ሉም።
9እን​ጥ​ሽ​ታው ብል​ጭ​ታን ያወ​ጣል፥
ዐይ​ኖ​ቹም እንደ አጥ​ቢያ ኮከብ ናቸው።
10ከአፉ የሚ​ቃ​ጠል መብ​ራት ይወ​ጣል
የእ​ሳ​ትም ፍን​ጣሪ ይረ​ጫል።
11የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ
ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።
12እስ​ት​ን​ፋሱ እንደ ፍም ናት።
ነበ​ል​ባ​ልም ከአፉ ይወ​ጣል።
13በአ​ን​ገቱ ኀይል ታድ​ራ​ለች፤
ለሚ​ያ​የ​ውም በፊቱ ሞት ይው​ላል።
14የአ​ካሉ ሥጋም የተ​ነ​ባ​በረ ነው፤
ጎጂ ነገ​ርን ቢያ​ፈ​ስ​ሱ​በ​ትም አይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም፤
15ልቡ እንደ ዋሻ ድን​ጋይ የደ​ነ​ደነ ነው፤
እንደ ወፍጮ ድን​ጋ​ይም የጸና ነው።
16በተ​መ​ለ​ሰም ጊዜ አራ​ዊ​ትና እን​ስሳ ይፈ​ራሉ፥
በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ይሸ​በ​ራሉ።
17ሰይ​ፍና ጦር፥ ፍላ​ጻና መው​ጊ​ያም ቢያ​ገ​ኙት
ምንም አያ​ደ​ር​ጉ​ትም።
18በእ​ርሱ ዘንድ መው​ጊ​ያና የብ​ረት ልብስ እንደ ገለባ ናቸው።
ናስም እንደ ነቀዘ እን​ጨት ነው።
19የናስ ፍላጻ ሊበ​ሳው አይ​ች​ልም፤
የወ​ን​ጭፍ ድን​ጋ​ዮ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ እንደ ገለባ ናቸው።
20ድጅኖ ቀሰም ይመ​ስ​ለ​ዋል
በታ​ላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች ላይ ይሥ​ቃል።
21መኝ​ታው#ዕብ. “ታቹ” ይላል። እንደ ስለ​ታም ድን​ጋይ ነው፤
የባ​ሕር ወርቅ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ጭቃ ነው።
22ቀላ​ይ​ዋን እንደ ብረት ድስት ያፈ​ላ​ታል፤
ባሕ​ሩም ምድረ በዳ ይመ​ስ​ለ​ዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ባሕ​ሩ​ንም እንደ ሽቱ ማሰሮ ያደ​ር​ገ​ዋል” ይላል።
23የሲ​ኦ​ልም ጥል​ቀት እንደ ምርኮ ነው።
ቀላ​ዩ​ንም እንደ መመ​ላ​ለሻ መን​ገድ ያደ​ር​ጋል።
24በተ​ፈ​ጠረ ጊዜ መላ​እ​ክቴ የሣ​ቁ​በት፥
እንደ እርሱ ያለ በም​ድር ላይ ምንም የለም።
25ከፍ ያለ​ውን ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታል፤
በውኃ ውስ​ጥም ላሉ ሁሉ ንጉሥ ነው።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in