መጽሐፈ ኢዮብ 41
41
1አትፈራምን? ለእኔ አዘጋጅተሃልና።#በዕብራይስጥ ይለያል።
የሚቃወመኝስ ማን ነው?
2የሚከራከረኝና በሕይወት የሚኖርስ ማን ነው?
ከሰማይ በታች ያለውም ሁሉ የእኔ ነው።
3ስለ እርሱ ዝም አልልም፥
የኀይል ቃልም እንደ እርሱ ያለውን ይቅር ይለዋል።
4የፊቱን መጋረጃ ማን ይገልጣል?#በዕብራይስጥ ይለያል።
ወደ ደረቱ መጋጠሚያ ውስጥስ ማን ይገባል?
5የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው?
በጥርሶቹ ዙሪያም ግርማ አለ።
6አንጀቶቹ የናስ አራዊት ናቸው፤
የቆዳውም ጽናት እንደ ዓለት ድንጋይ ነው።
7እርስ በርሳቸው የተጣበቁ ናቸውና፥
ነፋስም በመካከላቸው መግባት አይችልም።
8ሰውን ከወንድሙ ጋር አንድ ያደርጋል፤
እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፤ ሊለያዩም አይችሉም።
9እንጥሽታው ብልጭታን ያወጣል፥
ዐይኖቹም እንደ አጥቢያ ኮከብ ናቸው።
10ከአፉ የሚቃጠል መብራት ይወጣል
የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
11የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ
ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
12እስትንፋሱ እንደ ፍም ናት።
ነበልባልም ከአፉ ይወጣል።
13በአንገቱ ኀይል ታድራለች፤
ለሚያየውም በፊቱ ሞት ይውላል።
14የአካሉ ሥጋም የተነባበረ ነው፤
ጎጂ ነገርን ቢያፈስሱበትም አይንቀሳቀስም፤
15ልቡ እንደ ዋሻ ድንጋይ የደነደነ ነው፤
እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጸና ነው።
16በተመለሰም ጊዜ አራዊትና እንስሳ ይፈራሉ፥
በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ይሸበራሉ።
17ሰይፍና ጦር፥ ፍላጻና መውጊያም ቢያገኙት
ምንም አያደርጉትም።
18በእርሱ ዘንድ መውጊያና የብረት ልብስ እንደ ገለባ ናቸው።
ናስም እንደ ነቀዘ እንጨት ነው።
19የናስ ፍላጻ ሊበሳው አይችልም፤
የወንጭፍ ድንጋዮችም በእርሱ ዘንድ እንደ ገለባ ናቸው።
20ድጅኖ ቀሰም ይመስለዋል
በታላላቅ ድንጋዮች ላይ ይሥቃል።
21መኝታው#ዕብ. “ታቹ” ይላል። እንደ ስለታም ድንጋይ ነው፤
የባሕር ወርቅ ሁሉ በእርሱ ዘንድ እንደማይቈጠር ጭቃ ነው።
22ቀላይዋን እንደ ብረት ድስት ያፈላታል፤
ባሕሩም ምድረ በዳ ይመስለዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ባሕሩንም እንደ ሽቱ ማሰሮ ያደርገዋል” ይላል።
23የሲኦልም ጥልቀት እንደ ምርኮ ነው።
ቀላዩንም እንደ መመላለሻ መንገድ ያደርጋል።
24በተፈጠረ ጊዜ መላእክቴ የሣቁበት፥
እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ ምንም የለም።
25ከፍ ያለውን ሁሉ ይመለከታል፤
በውኃ ውስጥም ላሉ ሁሉ ንጉሥ ነው።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 41: አማ2000
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፈ ኢዮብ 41
41
1አትፈራምን? ለእኔ አዘጋጅተሃልና።#በዕብራይስጥ ይለያል።
የሚቃወመኝስ ማን ነው?
2የሚከራከረኝና በሕይወት የሚኖርስ ማን ነው?
ከሰማይ በታች ያለውም ሁሉ የእኔ ነው።
3ስለ እርሱ ዝም አልልም፥
የኀይል ቃልም እንደ እርሱ ያለውን ይቅር ይለዋል።
4የፊቱን መጋረጃ ማን ይገልጣል?#በዕብራይስጥ ይለያል።
ወደ ደረቱ መጋጠሚያ ውስጥስ ማን ይገባል?
5የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው?
በጥርሶቹ ዙሪያም ግርማ አለ።
6አንጀቶቹ የናስ አራዊት ናቸው፤
የቆዳውም ጽናት እንደ ዓለት ድንጋይ ነው።
7እርስ በርሳቸው የተጣበቁ ናቸውና፥
ነፋስም በመካከላቸው መግባት አይችልም።
8ሰውን ከወንድሙ ጋር አንድ ያደርጋል፤
እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፤ ሊለያዩም አይችሉም።
9እንጥሽታው ብልጭታን ያወጣል፥
ዐይኖቹም እንደ አጥቢያ ኮከብ ናቸው።
10ከአፉ የሚቃጠል መብራት ይወጣል
የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
11የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ
ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
12እስትንፋሱ እንደ ፍም ናት።
ነበልባልም ከአፉ ይወጣል።
13በአንገቱ ኀይል ታድራለች፤
ለሚያየውም በፊቱ ሞት ይውላል።
14የአካሉ ሥጋም የተነባበረ ነው፤
ጎጂ ነገርን ቢያፈስሱበትም አይንቀሳቀስም፤
15ልቡ እንደ ዋሻ ድንጋይ የደነደነ ነው፤
እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጸና ነው።
16በተመለሰም ጊዜ አራዊትና እንስሳ ይፈራሉ፥
በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ይሸበራሉ።
17ሰይፍና ጦር፥ ፍላጻና መውጊያም ቢያገኙት
ምንም አያደርጉትም።
18በእርሱ ዘንድ መውጊያና የብረት ልብስ እንደ ገለባ ናቸው።
ናስም እንደ ነቀዘ እንጨት ነው።
19የናስ ፍላጻ ሊበሳው አይችልም፤
የወንጭፍ ድንጋዮችም በእርሱ ዘንድ እንደ ገለባ ናቸው።
20ድጅኖ ቀሰም ይመስለዋል
በታላላቅ ድንጋዮች ላይ ይሥቃል።
21መኝታው#ዕብ. “ታቹ” ይላል። እንደ ስለታም ድንጋይ ነው፤
የባሕር ወርቅ ሁሉ በእርሱ ዘንድ እንደማይቈጠር ጭቃ ነው።
22ቀላይዋን እንደ ብረት ድስት ያፈላታል፤
ባሕሩም ምድረ በዳ ይመስለዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ባሕሩንም እንደ ሽቱ ማሰሮ ያደርገዋል” ይላል።
23የሲኦልም ጥልቀት እንደ ምርኮ ነው።
ቀላዩንም እንደ መመላለሻ መንገድ ያደርጋል።
24በተፈጠረ ጊዜ መላእክቴ የሣቁበት፥
እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ ምንም የለም።
25ከፍ ያለውን ሁሉ ይመለከታል፤
በውኃ ውስጥም ላሉ ሁሉ ንጉሥ ነው።”
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in