መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 15
15
ለይሁዳ ነገድ የተሰጠ ርስት
1የይሁዳም ነገድ ድንበር በየወገናቸው ከኤዶምያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው። 2በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስከሚወስደው መንገድ ነበረ። 3ከዚያም በአቅረቢን ዐቀበት ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጺንም ይወጣል፤ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወጣል፤ በአስሮንም በኩል ያልፋል፤ ወደ ሰራዳም ይወጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕራብም ይዞራል። 4ወደ አጽሞንም ያልፋል፤ በግብፅም ሸለቆ በኩል ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። 5በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤ 6ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤ 7ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤ 8ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወጣል፤ ድንበሩም በሰሜን በኩል በራፋይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባሕር በኩል ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ይወጣል፤ 9ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል። 10ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል። 11ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 12በባሕር በኩል ያለው ድንበራቸውም እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
ካሌብ ኬብሮንንና ዳቤርን እንደ ያዘ
(መሳ. 1፥11-15)
13በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ድርሻውን ሰጠው፤ ኢያሱም የዔናቅ#ዕብ. “አርቦቅን የኤናቅ አባት” ይላል። ዋና ከተማ የሆነችውን የአርቦቅን ከተማ ሰጠው። እርስዋም ኬብሮን ናት። 14የዮፎኒ ልጅ ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለሚንና አካሚን ከዚያ አጠፋቸው። 15ከዚያም ካሌብ በዳቤር ሰዎች ላይ ዘመተ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ “ሀገረ መጻሕፍት” ነበረ። 16ካሌብም፥ “ሀገረ መጻሕፍትን ለሚመታ፥ ለሚይዛትም ልጄን አክሳን#ግእዙ “አስካ” ይላል። ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ” አለ። 17የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ልጁን አክሳንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። 18እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ “አባቴን እርሻ ልለምነው” ብላ አማከረችው፤ እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። 19እርስዋም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ” አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
የይሁዳ ነገድ ርስት
20በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።
21በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቤሴሌኤል፥ አራ፥ አሦር፤ 22ኤቃም፥ ሬግማ፥ አሩሔል፤ 23ቃዴስ፥ አሶርዮስም፤ ሚናን፤ 24በልማንና መንደሮቻቸውም፤ 25የአሴሮም ከተሞች እርስዋም አሶር ናት። 26ሲን፥ ሰላማዓ፥ ሞላዳ፤ 27ሴሪ፥ ቤፋላድ፤ 28ኮላሴዎል፥ ቤርሳቤሕና መንደሮቻቸው። 29ባላ፥ ባቆብና አሶም፤ 30ኤለቦሂዳድ፥ ቤቴልና ኤርማም፤ 31ሴቄላቅ፥ ማኬሪምር፥ ሴቱናቅ፤ 32ላቦስ ሳሌ፥ ኤርሞትም ሃያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
33በቆላው፥ አስጣል፥ ሳራዓ፥ አሳ፤ 34ራሜ፥ ጣኖ፥ ኢዱቶት፥ መሐንስ፤ 35ኤርሙት፥ ኤዶላም፥ ሜምብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤ 36ሴቃርም፥ ጋዴርና ሰፈሮችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
37ሴና፥ አዳሶን፥ ማጋዳልጋድ፤ 38አዶላል፥ መሴፋ፥ ይቃሩል፥ ለኪስ፤ 39በሴዶት ይዴሃ፥ ደልያም፤ 40ኮብራ፥ ማኬስ፥ መሐኮስም፤ 41ጌዶር፥ በጋድያል፥ ኖማን፥ መቄዶም፥ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
42ሌምና፥ ኤተቅ፥ አኖክ፥ 43ኢድና ናሲብም፤ 44ኤላም፥ አቁዛም፥ ኬዜብ ቴርሳ፥ ኤሎምም፥ ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው።
45አቃሮን ከመንደሮችዋና ከመሰማሪያዎችዋ ጋር። 46ከአቃሮንና ከጌምና ጀምሮ በአሴዶት አቅራቢያ ያሉ ሁሉና መንደሮቻቸው፤
47አሴያዶት መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም፥ ጋዛም መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕርም ወሰኑ ነው።
48የሳምር ተራራዎች ፥ ኢዩቴር፥ ሦካ፤ 49ሬና፥ የመጽሐፍ ሀገር የሆነች ዳቤር፤ 50አኖን፥ ሴቄማ፥ ኤሳማም፤ 51ጎሶም ከሉም፥ ከናም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
52ኤሬም፥ ሬምና፥ ሶማ፤ 53ኢያማይን፥ ቤታቁም፥ ፋቁሕ፤ 54ኤውማ፥ የአርቦቅ ከተማ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ሶሬት፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። 55ማሖር፥ ኬርሜል፥ አዚብ፥ ኢጣን፤ 56ኢያሬዬል፥ ኢያሪቅም፥ ዘቃይንም፤ 57ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
58አሌዋ፥ ቤተሱር፥ ጌዶር፤ 59ማዕራት፥ ቤትአኖት፥ ኤልትቆን፥ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
60ቴቆ፥ ኤፍራታ፥ ይኽችውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎርም፥ ኤጣንም፥ ቁሎን፥ ጠጦንም፥ ሶብሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ ቅርያትበኣል፥ ይኽችውም የኢያርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
61ባዳርጊስ፥ ተራብዐምም፥ ኤኖን፤ ሴኬዎዛን፥ 62ናፍላዛንና ከተሞቻቸው፥ ሳዶን፥ አቃዴስ፥ ሰባት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
63በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 15: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: