YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 18

18
የቀ​ሪው ርስት አከ​ፋ​ፈል
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው። 2ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት ያል​ተ​ካ​ፈሉ ሰባት ነገድ ቀር​ተው ነበር። 3ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር እን​ዳ​ት​ወ​ር​ሱ​አት እስከ መቼ ድረስ ታቈ​ዩ​አ​ታ​ላ​ችሁ? 4ከየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎ​ችን አምጡ፥#ዕብ. “እኔም እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ” ብሎ ይጨ​ም​ራል። ተነ​ሥ​ተ​ውም ሀገ​ሪ​ቱን ይዙ​ሩ​አት፤ ለመ​ክ​ፈ​ልም እን​ዲ​ያ​መች ገል​ጠው ይጻ​ፉ​አት፤ ወደ እኔም ይመ​ለ​ሳሉ። 5በሰ​ባ​ትም ክፍል ይከ​ፍ​ሉ​ታል፤ ይሁዳ በደ​ቡብ በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣል፤ የዮ​ሴ​ፍም ልጆች በሰ​ሜን በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣሉ። 6እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤#ዕብ. “ ጻፉት የጻ​ፋ​ች​ሁ​ት​ንም ...” ይላል። ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 7ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”
8ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ኢያ​ሱም ምድ​ሩን ሊጽፉ የሄ​ዱ​ትን፥ “ሂዱ፤ ምድ​ሩ​ንም ዞራ​ችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመ​ለሱ፤ በዚ​ህም በሴሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። 9ሰዎ​ቹም ሄደው ምድ​ሩን ዞሩ፥ አዩ​ትም፤ እንደ ከተ​ሞ​ችም በሰ​ባት ክፍል ከፈ​ሉት፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፉት፤ ወደ ኢያ​ሱም አመጡ።#ዕብ. “ ኢያ​ሱም ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ሴሎ ተመ​ለሱ” ይላል። 10ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።#ዕብ. “በዚ​ያም ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እንደ ክፍ​ሎ​ቻ​ቸው ምድ​ሩን ከፈለ” የሚል ይጨ​ም​ራል።
ለብ​ን​ያም ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
11የብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዕጣ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው በቅ​ድ​ሚያ ወጣ፤ የዕ​ጣ​ቸ​ውም ዳርቻ በይ​ሁዳ ልጆ​ችና በዮ​ሴፍ ልጆች መካ​ከል ወጣ። 12በሰ​ሜን በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀመረ፤ ድን​በ​ሩም ከኢ​ያ​ሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚ​ያም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መው​ጫ​ውም የቤ​ቶን ምድ​ብ​ራ​ይ​ጣስ ነበረ። 13ድን​በ​ሩም ከዚያ በደ​ቡብ በኩል ቤቴል ወደ​ም​ት​ባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድን​በ​ሩም በታ​ች​ኛው ቤቶ​ሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአ​ጣ​ሮ​ቶ​ሬክ ወረደ። 14ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ። 15የደ​ቡ​ብም ዳርቻ ከቅ​ር​ያ​ታ​ርም መጨ​ረሻ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም በጋ​ሲን ላይ ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ። 16ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ተራራ መጨ​ረሻ ወረደ፤ እር​ሱም በራ​ፋ​ይም ሸለቆ በሰ​ሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያ​ቡስ ዳር በደ​ቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምን​ጭም ወረደ። 17ወደ ቤተ​ሳ​ሚ​ስም ምንጭ ያል​ፋል፤ በኢ​ታ​ሚም አቀ​በት ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ኬል​ዩት ይገ​ባል፤ ወደ ሮቤ​ልም ልጅ ወደ ቤዎን ድን​ጋይ ይወ​ር​ዳል፤ 18በሰ​ሜ​ንም በኩል ወደ ቤተ ራባ ጀርባ ያል​ፋል። በመ​ስ​ዕም ወደ ባሕር መን​ገድ ይወ​ር​ዳል፤ 19የድ​ን​በ​ራ​ቸ​ውም ፍጻሜ በሰ​ሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደ​ር​ሳል፤ በደ​ቡ​ብም በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ዮር​ዳ​ኖስ ነው። ይህም በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በር ነው። 20በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ድን​በሩ ዮር​ዳ​ኖስ ነበረ። ይህ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዳርቻ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች ርስት ነበረ።
21የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ ከተ​ሞች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ኢያ​ሪኮ፥ ቤት​ሖ​ግሊ፥ ዐመ​ቀ​ስስ፤ 22ቤተ ባራ፥ ሰራ፥ ቤስና፤ 23አኢን፥ ፋራ፥ ኤፍ​ራ​ታም፥ 24ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። 25ገባ​ዖን፥ ራማ፥ ብኤ​ሮት፤ 26ማሴማ፥ ቤሮን፥ አሞቂ፥ 27ቤራ፥ ቃፋን፥ ናቃና፥ ሴሌ​ቃን፥ ታራ​ኤላ፤ 28ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ባል የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ከተ​ማና የኢ​ያ​ሪ​ሞን ከተማ ገባ​ዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። የብ​ን​ያም ልጆች ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in