YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 19

19
ለስ​ም​ዖን ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
1ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ ርስ​ታ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ ልጆች ርስት መካ​ከል ነበረ። 2ዕጣ​ቸ​ውም እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቤር​ሳ​ቤህ፥ ሰማህ፥ ቆሎ​ዶን፤ 3አር​ሳላ፥ ባላ፥ ኢያ​ሶ​ንም፤ 4ኤር​ቱላ፥ ቡላ፥ ሔር​ማም፤ 5ሴቄ​ላቅ፥ ቤተ​ማ​ኮ​ሬብ፥ ሰር​ሱ​ሲን፤ 6ቦታ​ሩ​ትና ሜዳ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤ 7ሬሞን፥ ቴልካ፥ ኢያ​ቴር፥ አሳ​ንም፥ አራት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤ 8እስከ ባሌቅ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ያሉ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባ​ሜት ላይ ወደ ደቡብ ያል​ፋል። የስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ። 9ከይ​ሁዳ ልጆች ክፍል የስ​ም​ዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛ​ባ​ቸው የስ​ም​ዖን ልጆች በር​ስ​ታ​ቸው መካ​ከል ወረሱ።
ለዛ​ብ​ሎን ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
10ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዛ​ብ​ሎን ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ድን​በር እስከ ኤሴ​ዴቅ ጎላ ነበረ፤ 11ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ማራ​ጌላ ይወ​ጣል፤ እስከ ቤተ ራባም ይደ​ር​ሳል፤ በኢ​ያ​ቃ​ንም ፊት ለፊት ወዳ​ለው ሸለ​ቆም ይደ​ር​ሳል፤ 12ከሴ​ዱ​ቅም ወደ ቤተ ሳሚስ ምሥ​ራቅ ወደ ካሲ​ሎ​ቴት ዳርቻ ይዞ​ራል፤ ወደ ዳቤ​ሮ​ትም ይወ​ጣል፤ ወደ ፋን​ጊም ይደ​ር​ሳል፤ 13ከዚ​ያም ወደ ጌቤሮ ምሥ​ራቅ ወደ ከታ​ሤም ከተማ ያል​ፋል፤ ወደ ሪና​ሞን ወደ ማታ​ር​ዮዛ ይወ​ጣል። 14ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል ወደ አሞት ይዞ​ራል፥ መው​ጫ​ውም በሐ​ናት በኩል በጌ​ፋ​ሄል ሸለቆ ነበረ። 15ቃጠ​ናት፥ ናባ​ሐል፥ ሲም​ዖን፥ ኢያ​ሪሆ፥ ቤቴ​ሜ​ንም፤ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።#“ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 16የዛ​ብ​ሎን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።
ለይ​ሳ​ኮር ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
17አራ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለይ​ሳ​ኮር ልጆች ወጣ። 18ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢይ​ዝ​ራ​ኤል፥ ከል​ሰ​ሉት፥ ሱሳን፤ 19አጊን፥ ሴዎ​ንና፥ ርሄቱ፥ 20አን​ከ​ሬት፥ ዳቤ​ሮት፥ ቂሶን፥ ሮቤስ፤ 21ሬማስ፥ ያዖን፥ ቶማን፥ ኤሜ​ሬቅ፥ ቤር​ሳ​ፌስ ነበረ። 22ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ወደ ታቦ​ርና ወደ ሰሌም፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ቤተ​ሳ​ሚስ ይደ​ር​ሳል፤ የድ​ን​በ​ራ​ቸው መው​ጫም ዮር​ዳ​ኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም።#“ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 23የይ​ሳ​ኮር ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።
ለአ​ሴር ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
24አም​ስ​ተ​ኛው ዕጣ ለአ​ሴር ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ። 25ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኤል​ኬት፥ ኤሌፍ፥ ቤቶቅ፥ ቂያፍ፤ 26አሊ​ሜ​ሌክ፥ አሜ​ሕል፥ ማሕሳ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም በኩል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ ወደ ሴዎ​ንና ሊበ​ናት ይደ​ር​ሳል፤ 27ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴ​ጌ​ነት ይዞ​ራል፤ በመ​ስ​ዕም በኩል ከዛ​ብ​ሎ​ንና ከጋይ ከይ​ፍ​ታ​ሕ​ኤል ይያ​ያ​ዛል ወደ ሳፍቱ ቤታ​ሜ​ሕና ወደ ኢን​ሂል ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኮባ ማሾ​ሜ​ልም ያል​ፋል፤ 28ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል። 29ድን​በ​ሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስ​ፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞ​ራል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ኢያ​ሴፍ ይዞ​ራል፤ መው​ጫ​ውም በሌ​ብና በኮ​ዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ 30አር​ኮብ፥ አፌቅ፥ ረአ​ውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም።#“ሃያ ሁለት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 31የአ​ሴር ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።
ለን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
32ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ። 33ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ላም፥ ከሞ​ላም፥ ከቤ​ሴ​ሜ​ይን፥ ከአ​ርሜ፥ ከና​ቦ​ቅና፥ ከኢ​ያ​ፍ​ታ​ሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መው​ጫ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ነበረ። 34ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አዝ​ኖ​ት​ታ​ቦር ይዞ​ራል፤ ከዚ​ያም ወደ ያቃና ይወ​ጣል፤ ከዚ​ያም በደ​ቡብ በኩል ወደ ዛብ​ሎን፤ በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም በፀ​ሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ይደ​ር​ሳል። 35የተ​መ​ሸ​ጉ​ትም የሲ​ዶና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጢ​ሮ​ሳ​ው​ያን” ይላል። ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማ​ታ​ዳ​ቄት፥ ቄሬት፥ 36አር​ሜት፥ አራ​ሂን፥ አሦር፥ 37ቃዴስ፥ አስ​ራ​ይስ፥ የአ​ሦር ምንጭ፥ 38ቄሮህ፥ ሚጋ​ላ​ህ​ሪም፥ ቤታ​ሚና፥ ቴስ​ሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መን​ደ​ሮ​ችና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው።#“ዐሥራ ዘጠኝ መን​ደ​ሮ​ችና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 39የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ ርስት እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው።#“ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ለዳን ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
40ሰባ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ። 41የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ሠራ​ሕት፥ አሳ፥ የሰ​መ​ውስ ከተማ፥ 42ሰሊ​ባን፥ አሞን፥ ሴላታ፥ 43ኤሎን፥ ቴም​ናታ፥ አቃ​ሮን፥ 44አል​ቃታ፥ ቤጌ​ቶን፥ ጌቤ​ላን፥ 45አዞር፥ ቤኔ​ቤ​ቃት፥ ጌት​ሬ​ሞን፤ 46በባ​ሕር በኩል በኢ​ዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያ​ራ​ቆን። 47የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ናቸው። የዳን ልጆ​ችም በተ​ራ​ራው ላይ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸ​ውም። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ወደ ሸለ​ቆ​ዎች ይወ​ርዱ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ላ​ቸ​ውም። ከእ​ነ​ር​ሱም ከር​ስ​ታ​ቸው ዳርቻ አንድ ክፍ​ልን ወሰዱ። 48የዳን ልጆ​ችም ሄደው ለኪ​ስን መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ቸ​ው​ንም ያዟት፤ በሰ​ይ​ፍም መቱ​አት። በው​ስ​ጥ​ዋም ተቀ​መጡ። ስሟ​ንም በአ​ባ​ታ​ቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩ​አት። አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም በኤ​ዶ​ምና በሰ​ላ​ሚን ለመ​ኖር ቀጠሉ። የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ በረ​ታች። ገባ​ሪ​ዎ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።
ለኢ​ያሱ የተ​ሰጠ ርስት
49ምድ​ሩ​ንም ሁሉ በየ​ድ​ን​በሩ ርስት እን​ዲ​ሆን ከፍ​ለው ከጨ​ረሱ በኋላ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርስት ሰጡት። 50በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት። 51ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገ​ዶች የአ​ባ​ቶች አለ​ቆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በዕጣ የተ​ካ​ፈ​ሉት ርስት ይህ ነው። ምድ​ሪ​ቱ​ንም መካ​ፈል ፈጸሙ። #“ምድ​ሪ​ቱ​ንም መካ​ፈል ፈጸሙ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in