YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 2

2
ኢያሱ ወደ ኢያ​ሪኮ ጉበ​ኞ​ችን እንደ ላከ
1የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ። 2ለኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሰላ​ዮች ሀገ​ራ​ች​ንን ሊሰ​ልሉ ወደ​ዚህ በሌ​ሊት ገቡ” ብለው ነገ​ሩት። 3የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። 4ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤#“ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 5በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው። 6እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር። 7ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።
8እነ​ዚ​ህም ሳይ​ተኙ ሴቲቱ ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰገ​ነቱ ወጣች። 9ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና። 10ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል። 11ይህ​ንም ነገር ሰም​ተን በል​ባ​ችን ደነ​ገ​ጥን፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር እርሱ አም​ላክ ነውና ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ከእኛ የአ​ን​ዱም እን​ኳን ነፍስ አል​ቀ​ረም። 12አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ።#“ምል​ክት ስጡኝ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም.። 13የአ​ባ​ቴን ቤት፥ እና​ቴ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ቼ​ንና ቤቴ​ንም ሁሉ፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አድኑ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ከሞት አድኑ።” 14ሰዎ​ቹም፥ “ሕይ​ወ​ታ​ች​ንን ስለ እና​ንተ አሳ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን” አሉ፤ እር​ስ​ዋም አለች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ ቸር​ነ​ት​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጉ​ል​ና​ላ​ችሁ።” ሰዎ​ቹም፥ “ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ባት​ገ​ልጪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ራ​ች​ሁን በእ​ው​ነት አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን ከአ​ንቺ ጋር ቸር​ነ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሏት።
15ቤቷም በከ​ተማ ቅጥር የተ​ጠጋ ነበ​ረና፥ እር​ስ​ዋም በቅ​ጥሩ ላይ ተቀ​ምጣ ነበ​ርና#“ቤቷም በከ​ተማ ቅጥር የተ​ጠጋ ነበ​ረና እር​ስ​ዋም በቅ​ጥሩ ላይ ተቀ​ምጣ ነበ​ርና” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በመ​ስ​ኮቱ በገ​መድ አወ​ረ​ደ​ቻ​ቸው። 16እር​ስ​ዋም፥ “የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወደ ተራ​ራው ሂዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ች​ሁም እስ​ከ​ሚ​መ​ለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰ​ው​ራ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ በኋ​ላም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው። 17ሰዎ​ቹም አሉ​አት፥ “እኛ ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን። 18እነሆ፥ እኛ ወደ ሀገሩ በገ​ባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወ​ረ​ድ​ሽ​በት መስ​ኮት በኩል እሰ​ሪው፤ አባ​ት​ሽ​ንም፥ እና​ት​ሽ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ሽ​ንም፥ የአ​ባ​ት​ሽ​ንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብ​ስቢ። 19ከቤ​ት​ሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚ​ወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እኛም ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን፤ ነገር ግን ከአ​ንቺ ጋር በቤ​ትሽ ውስጥ ያለ ቢሞት ደሙ በእኛ ላይ ነው። 20ነገር ግን ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ብት​ገ​ልጪ ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን።” 21እር​ስ​ዋም፥ “እንደ ቃላ​ችሁ ይሁን” አለች፤ አሰ​ና​በ​ተ​ቻ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ሄዱ፤ ቀዩ​ንም ፈትል በመ​ስ​ኮቱ በኩል አን​ጠ​ለ​ጠ​ለ​ችው።#“ቀዩ​ንም ፈትል በመ​ስ​ኮቱ በኩል አን​ጠ​ለ​ጠ​ለ​ችው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
22እነ​ር​ሱም ወጥ​ተው ወደ ተራ​ራው ሄዱ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና የሚ​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸ​ውም እስ​ኪ​መ​ለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀ​መጡ፤ በመ​ን​ገ​ዱም አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ውም። 23ሁለ​ቱም ጐል​ማ​ሶች ተመ​ለሱ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም ወር​ደው ተሻ​ገሩ፤ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደ​ረ​ሰ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አወ​ሩ​ለት። 24ኢያ​ሱ​ንም፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ሩን ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ከእኛ የተ​ነሣ ደነ​ገጡ” አሉት።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in