YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 20

20
መማ​ፀኛ ከተ​ሞች
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ በሙሴ ቃል የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ስጡ። 3ባለ​ማ​ወቅ ሳይ​ወ​ድድ ሰውን የገ​ደለ በዚያ ይማ​ፀን ዘንድ፥ ለእ​ና​ንተ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ሥሩ፤ ነፍስ የገ​ደለ ሰውም በአ​ደ​ባ​ባይ ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቀ​ርብ ድረስ በደም ተበ​ቃዩ አይ​ገ​ደል። 4ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ይማ​ፀ​ናል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነገ​ሩን ይና​ገ​ራል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ያገ​ቡ​ታል። የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ስፍራ ይሰ​ጡ​ታል። 5ባለ ደሙ ቢያ​ሳ​ድ​ደው፥ አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ጠ​ላው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ሕ​ተት ስለ ገደ​ለው ነፍሰ ገዳ​ዩን በእጁ አሳ​ል​ፈው አይ​ስ​ጡት። 6በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቆም ድረስ ፥ በዚ​ያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚ​ያች ከተማ ይቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ ከተ​ማ​ውም፥ ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣ​በ​ትም ከተማ ይገ​ባል።”
7በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ። 8በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ። 9በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in