YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 4

4
እስ​ራ​ኤል መታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዳ​ቆሙ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ከሕ​ዝቡ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ውሰድ፦ 3በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ#“የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ዐሥራ ሁለት ቀላል ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዲ​ያ​ነሡ እዘ​ዛ​ቸው፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ውሰ​ዱ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም ሌሊት በም​ታ​ድ​ሩ​በት ቦታ በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጠብ​ቋ​ቸው።”
4ኢያ​ሱም ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የታ​ወ​ቁ​ትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። 5ኢያ​ሱም አላ​ቸው፥ “በእ​ኔና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት#ዕብ. “ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት” ይላል። ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዕለፉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ቍጥር በት​ከ​ሻው ላይ አንድ አንድ ድን​ጋይ ከዚያ ይሸ​ከም። 6እነ​ዚ​ህም ምል​ክት ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥ ልጅ​ህን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ 7አንተ በም​ድር ሁሉ ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስን​ሻ​ገር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናሉ።”
8የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢያሱ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዳ​ዘ​ዘው” ይላል። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዮር​ዳ​ኖ​ስን አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እንደ አዘ​ዘው በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ቍጥር#“በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ቍጥር” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮች አን​ሥ​ተው ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወሰዱ፤ በዚ​ያም አኖ​ሩ​አ​ቸው። 9ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ። 10ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ። 11ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ#ግሪክ ሰባ ሊ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕጉ ታቦት” ሲል ዕብ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት” ይላል። ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች#ዕብ. “ካህ​ናቱ” ይላል። በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ። 12ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ። 13አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ። 14በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 16“የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት” ይላል። የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ እን​ዲ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው።” 17ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውጡ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። 18የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በወጡ ጊዜ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም የብስ በረ​ገጡ ጊዜ፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ተወ​ር​ውሮ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።
19ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ። 20ኢያ​ሱም ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ዐሥራ ሁለ​ቱን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ል​ገላ አቆ​ማ​ቸው። 21ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብለው በሚ​ጠ​ይ​ቋ​ችሁ ጊዜ፥ 22ለል​ጆ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ትነ​ግ​ሯ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፦ ‘እስ​ራ​ኤል ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን በደ​ረቅ ተሻ​ገረ፤’ 23እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ከፊ​ታ​ችን እን​ዳ​ደ​ረቀ እን​ዲሁ እስ​ክ​ን​ሻ​ገር ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ ከፊ​ታ​ችን አደ​ረቀ። 24ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ጠን​ካራ እንደ ሆነች የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ያ​ውቁ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ራው ሁሉ እን​ድ​ት​ፈሩ ነው።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in