YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7

7
የአ​ካን በደል
1የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን እርም በሆ​ነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እር​ሱም የከ​ርሚ ልጅ፥ የዘ​ን​በሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆ​ነው ነገር ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።
2ኢያ​ሱም ከቤ​ቴል በም​ሥ​ራቅ በኩል በቤ​ት​አ​ዊን አጠ​ገብ#“በቤት አዊን አጠ​ገብ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወዳ​ለ​ችው ወደ ጋይ ሰዎ​ችን ከኢ​ያ​ሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይ​ንም ሰልሉ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹም ወጡ፤ ጋይ​ንም ሰለሉ። 3ወደ ኢያ​ሱም ተመ​ል​ሰው፥ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥ​ተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይ​ውጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ​ዚያ አት​ው​ሰድ፤ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውና” አሉት። 4ሦስት ሺህ ያህል ሰዎ​ችም ወደ​ዚያ ወጡ፤ የጋ​ይም ሰዎች አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም ሸሹ። 5የጋይ ሰዎ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ሠላሳ ስድ​ስት ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀም​ረው እስከ አጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ በቍ​ል​ቍ​ለ​ቱም ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሕ​ዝ​ቡም ልብ ደነ​ገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።
6ኢያ​ሱም ልብ​ሱን ቀደደ፤ እር​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ። 7ኢያ​ሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን፥ ታጠ​ፋ​ንም ዘንድ አገ​ል​ጋ​ይህ ይህን ሕዝብ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ለምን አሻ​ገረ? በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​ም​ጠን በኖ​ርን ነበር እኮ! 8ጌታ ሆይ! እስ​ራ​ኤል ጀር​ባ​ውን ወደ ጠላ​ቶቹ ከመ​ለሰ እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? 9ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖሩ ሁሉ ሰም​ተው ይከ​ብ​ቡ​ናል፤ ከም​ድ​ርም ያጠ​ፉ​ናል፤ ለታ​ላቁ ስም​ህም የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው?”
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “ለምን በግ​ን​ባ​ርህ ተደ​ፍ​ተ​ሃል? ተነሥ! 11ሕዝቡ በድ​ለ​ዋል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሰ​ዋል፤ እርም ከሆ​ነ​ውም ነገር ሰር​ቀው ወሰዱ፤ በዕ​ቃ​ቸ​ውም ውስጥ ሸሸ​ጉት። 12ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት መቆም አይ​ች​ሉም፤ የተ​ረ​ገሙ ስለ​ሆኑ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ይሸ​ሻሉ፤ እርም የሆ​ነ​ው​ንም ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ካላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከዚህ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር አል​ሆ​ንም። 13ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ። 14ነገም በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖቹ ይቀ​ር​ባል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ወገን በየ​ቤተ ሰቦቹ ይቀ​ር​ባል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ለ​የው ቤተ ሰብ በየ​ሰዉ ይቀ​ር​ባል። 15ምል​ክት የታ​የ​በት ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ በደል አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ እር​ሱና ያለው ሁሉ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ።”
16ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በየ​ነ​ገ​ዶ​ቻ​ቸው ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳም ነገድ ላይ ምል​ክት ታየ፤ 17የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች ተለዩ፤ በዛ​ራም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዛ​ራም ወገን በየ​ቤተ ሰቡ ተለየ፤ 18በዘ​ን​በ​ሪም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዘ​ን​በ​ሪም ቤተ ሰብ እያ​ን​ዳ​ንዱ ተለየ፤ ከይ​ሁ​ዳም ወገን በሆነ በከ​ርሚ ልጅ በዘ​ን​በሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአ​ካን ላይ ምል​ክት ታየ። 19ኢያ​ሱም አካ​ንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ስጥ፤ ለእ​ር​ሱም ተና​ዘዝ፤ ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንም ንገ​ረኝ፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ኝም” አለው። 20አካ​ንም መልሶ ኢያ​ሱን፥ “በእ​ው​ነት በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ያ​ለሁ፤ እን​ዲ​ህና እን​ዲ​ህም አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ። 21በዘ​ረፋ መካ​ከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛ​ኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመ​ኘ​ኋ​ቸው፤ ወሰ​ድ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ሆም በድ​ን​ኳኔ ውስጥ በመ​ሬት ተሸ​ሽ​ገ​ዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።
22ኢያ​ሱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ወደ ሰፈ​ርም ወደ ድን​ኳኑ ሮጡ፤ እነ​ሆም እርሱ በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ተደ​ብቆ፥ ብሩም በበ​ታቹ ነበረ። 23ከድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ አው​ጥ​ተው ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ አመ​ጡት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ም​ፊት አኖ​ሩት። 24ኢያ​ሱም#ዕብ. “እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ” የሚል ይጨ​ም​ራል። የዛ​ራን ልጅ አካ​ንን፥ ብሩ​ንም፥ ልብ​ሱ​ንም፥ ልሳነ ወር​ቁ​ንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በሬ​ዎ​ቹ​ንም፥ አህ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ በጎ​ቹ​ንም፥ ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ ንብ​ረ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ ዔሜ​ቃ​ኮር ወሰደ።#“ዔሜ​ቃ​ኮር” በዕብ. የአ​ኮር ሽለቆ ማለት ነው። 25ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤#“በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው። 26በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in