የሉቃስ ወንጌል 21
21
ሁለት መሐለቅ ስለ አገባችው ድሃ ሴት
1በሙዳየ ምጽዋቱ መባቸውን የሚያገቡ ባለጠጎችን አየ። 2አንዲት ድሃ መበለትም ሁለት መሐለቅ ስታስገባ አየ። 3እንዲህም አላቸው፥ “እውነት እላችኋለሁ፥ ይህቺ ድሃ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብዝታ ለእግዚአብሔር መባ አገባች። 4እነዚህ ሁሉ ከተረፋቸው ለእግዚአብሔር መባ አግብተዋልና፤ ይህቺ ግን ከድህነቷ ያላትን ጥሪቷን ሁሉ አገባች።”
ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ ቤተ መቅደስ መፍረስ
5ስለ ቤተ መቅደስም ድንጋዩ ያማረ ነው፥ አሠራሩም ያጌጠ ነው የሚሉት ነበሩ። 6እንዲህም አላቸው፥ “ይህን ታያላችሁን? በእዚህ ቦታ ድንጋይ በድንጋይ ላይ የማይተውበትና ሳይፈርስ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል።” 7እነርሱም፥ “መምህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደረጋል? ይህስ የሚሆንበት ጊዜው፥ ምልክቱስ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። 8እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ፤ ጊዜውም ደርሶአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና እንዳያስቱአችሁ ተጠንቀቁ፤ እነርሱንም ተከትላችሁ አትሂዱ። 9ጦርነትንና ጠብን፥ ክርክርንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ አስቀድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን ወዲያው የሚፈጸም አይደለም።”
10እንዲህም አላቸው፥ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ነገሥታትም በነገሥታት ላይ ይነሣሉ። 11በየሀገሩ ታላቅ የምድር መነዋወጥና ራብ፥ በሰውም ላይ በሽታና ፍርሀት ይመጣል፤ በሰማይም ታላቅ ምልክት ይሆናል። 12ከዚህም ሁሉ አስቀድሞ ይይዙአችኋል፤ ወደ አደባባዮችም ይወስዱአችኋል፤ ያሳድዱአችኋል፤ ያስሩአችኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ መሳፍንት ይወስዱአችኋል። 13ይህም በእነርሱ ላይ ምስክር ይሆንባቸዋል። 14#ሉቃ. 12፥11-12። ዕወቁ፤ የምትናገሩትንም በልባችሁ አታስቡ። 15በእናንተ ላይ የሚነሡ ሊመልሱላችሁና ሊከራከሯችሁ እንዳይችሉ እኔ አፍንና ጥበብን እሰጣችኋለሁ። 16ወላጆቻችሁና ወንድሞቻችሁ፥ ወዳጆቻችሁና ባልንጀሮቻችሁ አሳልፈው ይሰጡአችኋል። 17ሁሉም ስለ ስሜ ይጠሉአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም። 18ነገር ግን ከራስ ጠጕራችሁ አንዲቱ እንኳ አትጠፋም። 19በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ገንዘብ ታደርጓታላችሁ።
ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት መድረስ
20“ኢየሩሳሌምን ጭፍሮች ከብበዋት ባያችሁ ጊዜ ጥፋቷ እንደ ደረሰ ዕወቁ። 21ያንጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራ ይሽሹ፤ በመካከልዋ ያሉም ከእርስዋ ይውጡ፤ በአውራጃዎችዋ ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ። 22#ሆሴዕ 9፥7። በእርስዋ ላይ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እርስዋን የሚበቀሉበት ጊዜዋ ነውና። 23ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀነሱና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ በምድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ መቅሠፍት ይሆናልና። 24በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ፤ በአሕዛብም ሁሉ ይማረካሉ፤ የአሕዛብ ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ይረግጡአታል።
ስለ ክርስቶስ መምጣትና ስለ ምልክቶቹ
25 #
ኢሳ. 13፥10፤ ሕዝ. 32፥7፤ ኢዩ. 2፥31፤ ራእ. 6፥12-13። “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤#“ከዋክብትም ከሰማይ ወደ ምድር ይወድቃሉ” የሚል በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ ይገኛል። ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ። 26በዓለም ላይ ከሚመጣው ፍርሀትና ሽብር የተነሣም የሰዎች ነፍስ ትዝላለች፤ ያንጊዜ የሰማያት ኀይል ይናወጣልና። 27#ዳን. 7፥13፤ ራእ. 1፥7። ያንጊዜም በሰማይ ደመና፥ በፍጹም ኀይልና ክብር ሲመጣ የሰውን ልጅ ያዩታል። 28ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅንታችሁ ተመልከቱ፤ ራሳችሁንም አንሡ፤ የሚያድናችሁ መጥቶአልና።”
29ምሳሌም መስሎ እንዲህ አላቸው፥ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ። 30ለምልመውም ያያችኋቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታውቃላችሁ። 31እንዲሁ እናንተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ደረሰች ዕወቁ። 32እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪደረግ ድረስ ይህቺ ትውልድ አታልፍም። 33ሰማይና ምድር ያልፋል፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
ትምህርትና ምክር
34“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች። 35በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ተዘረጋች ወጥመድ ትደርሳለችና። 36እንግዲህ ከዚህ ከሚመጣው ሁሉ በጸሎታችሁ ማምለጥ እንድትችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እንድትቆሙ ሁልጊዜ ትጉ።”
በደብረ ዘይት ስለ ማደሩ
37 #
ሉቃ. 19፥47። ቀን ቀን በመቅደስ#በግእዙ “በምኵራብ” ይላል። ያስተምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚባለው ተራራ ያድር ነበር። 38ሕዝቡም ሁሉ ቃሉን ሊሰሙ እርሱ ወዳለበት ወደ መቅደስ ማልደው ይሄዱ ነበር።
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 21: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: