YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 10

10
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ፤
ነፍ​ሴን፥ እንደ ወፍ ወደ ተራ​ሮች ተቅ​በ​ዝ​በዢ እን​ዴት ትሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ?
2ኀጢ​አ​ተ​ኞች እነሆ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረ​ዋ​ልና፥
ፍላ​ጻ​ቸ​ው​ንም በአ​ው​ታር አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋ​ልና፥
ልበ ቅኖ​ቹን በስ​ውር ይነ​ድፉ ዘንድ።
3አንተ የሠ​ራ​ኸ​ውን እነሆ፥ እነ​ርሱ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤
ጻድቅ ግን ምን አደ​ረገ?
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቤተ መቅ​ደሱ ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋኑ በሰ​ማይ ነው፤
ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤
ቅን​ድ​ቦ​ቹም የሰው ልጆ​ችን ይመ​ረ​ም​ራሉ።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ይመ​ረ​ም​ራል፤
ዐመ​ፃን የወ​ደ​ዳት ግን ነፍ​ሱን ጠል​ቶ​አል።
6ወጥ​መድ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይዘ​ን​ባል፤
እሳ​ትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋ​ስም የጽ​ዋ​ቸው እድል ፋንታ ነው።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም ይወ​ድ​ዳል፤
ቅን​ነት ግን ፊቱን ታየ​ዋ​ለች።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in