መዝሙረ ዳዊት 14
14
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥
በልቡም እውነትን የሚናገር።
3በአንደበቱ የማይሸነግል፥
በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥
ዘመዶቹንም የማያሰድብ።
4ኀጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥
እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥
ለባልንጀራው ምሎ የማይከዳ።
5ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥
በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል።
እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 14: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in