መዝሙረ ዳዊት 19
19
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1በመከራህ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤
የያዕቆብ አምላክ ስምም ይቁምልህ።
2ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥
ከጽዮንም ይቀበልህ።
3መሥዋዕትህን#ዕብ. “ቍርባን” ይላል። ያስብልህ፤
ቍርባንህንም#ዕብ. “የሚቃጠል መሥዋዕት” ይላል። ያለምልምልህ።
4እግዚአብሔር እንደ ልብህ ይስጥህ
ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።
5በማዳንህ ደስ ይለናል፤
በእግዚአብሔር በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤
ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
6እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ ዐወቅሁ፤
ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል
በቀኙ የማዳን ኀይል።
7እነዚያ በፈረሶችና በሰረገላዎች ይታመናሉ፤
እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤
እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
9አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥
በምንጠራህም ቀን ስማን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 19: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in