YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 2

2
ትን​ቢት ስለ ክር​ስ​ቶስ
1አሕ​ዛብ ለምን ዶለቱ?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጕ​ረ​መ​ረሙ” ይላል።
ወገ​ኖ​ችስ ለምን ከንቱ ይና​ገ​ራሉ?
2የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተነሡ፥
አለ​ቆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ
እን​ዲህ ሲሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።
3“ማሰ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ከእኛ እን​በ​ጥስ፥
ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ከእኛ ላይ እን​ጣል።”
4በሰ​ማይ የሚ​ኖር እርሱ ይሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሣ​ለ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።
5በዚ​ያን ጊዜ በቍ​ጣው ይና​ገ​ራ​ቸ​ዋል፥
በመ​ዓ​ቱም ያው​ካ​ቸ​ዋል።
6እኔ ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ#ዕብ. “እኔ ንጉ​ሤን ሾምሁ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ርሱ ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ” ይላል። ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ
በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራው በጽ​ዮን ላይ።
7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥
እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።
8ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ
የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።
9በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥
እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”
10አሁ​ንም እና​ንት ነገ​ሥ​ታት፥ ልብ አድ​ርጉ፤
እና​ንት የም​ድር ፈራ​ጆ​ችም፥ ተገ​ሠጹ።
11ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ር​ሀት ተገዙ፥
በረ​ዓ​ድም ደስ ይበ​ላ​ችሁ።
12ጥበ​ብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተግ​ሣ​ጽን” ሲል ዕብ. “ወል​ድን ሳሙት” ይላል። አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥
እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥
ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥
በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in