YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 24

24
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ።
2አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ፈር፤
ጠላ​ቶቼ በእኔ አይ​ሣ​ቁ​ብኝ።
3አን​ተን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ አያ​ፍ​ሩ​ምና።
በከ​ንቱ የሚ​በ​ድሉ ሁሉ ዘወ​ትር ይፈሩ።
4አቤቱ፥ መን​ገ​ድ​ህን አመ​ል​ክ​ተኝ፤
ፍለ​ጋ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።
5በእ​ው​ነ​ትህ ምራኝ፤ አስ​ተ​ም​ረ​ኝም፤
አንተ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ነህና፥
ዘወ​ት​ርም አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።
6አቤቱ፥ ቸር​ነ​ት​ህን ዐስብ፥
ምሕ​ረ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
7የል​ጅ​ነ​ቴን ኀጢ​አ​ትና ስን​ፍ​ና​የን አታ​ስ​ብ​ብኝ።
አቤቱ፥ ስለ ቸር​ነ​ትህ ብዛት፥
እንደ ምሕ​ረ​ትህ ዐስ​በኝ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ጻድ​ቅም ነው፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቅን” ይላል።
ስለ​ዚህ የሚ​ሳ​ሳ​ቱ​ትን በመ​ን​ገድ ይመ​ራ​ቸ​ዋል።#ዕብ. “ኀጢ​አ​ተ​ኞች” ይላል።
9ለየ​ዋ​ሃን ፍር​ድን ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በፍ​ርድ ይመ​ራል” ይላል።
ለየ​ዋ​ሃን መን​ገ​ድን ያመ​ለ​ክ​ታ​ቸ​ዋል።
10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ ሁሉ ይቅ​ር​ታና እው​ነት ነው፤
ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምስ​ክ​ሩን ለሚ​ፈ​ልጉ።
11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ብለህ፥
ኀጢ​አ​ቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፥ ብዙ ነውና።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ማን ነው?
እርሱ በሚ​መ​ር​ጠው መን​ገድ ይመ​ራ​ዋል።
13ነፍሱ በመ​ል​ካም ታድ​ራ​ለች፥
ዘሩም ምድ​ርን ይወ​ር​ሳል።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ኀይ​ላ​ቸው ነው፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ለሚ​ጠ​ሩት ነው።
ሕጉ​ንም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል።
15ዐይ​ኖቼ ሁል​ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸው፤
እርሱ እግ​ሮ​ችን ከወ​ጥ​መድ ያወ​ጣ​ቸ​ዋ​ልና፥
16ፊት​ህን ወደ እኔ አድ​ርግ ማረ​ኝም፥
እኔ ብቸ​ኛና ድሃ ነኝና።
17የልቤ ኀዘን ብዙ ነው፤
ከጭ​ን​ቀቴ አው​ጣኝ።
18ድካ​ሜ​ንና መከ​ራ​ዬን እይ፥
ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19ጠላ​ቶቼ እንደ በዙ እይ፥
በግ​ፍም ጥልን ጠል​ተ​ው​ኛል።
20ነፍ​ሴን ጠብ​ቃት አድ​ና​ትም፥
አን​ተን ታም​ኛ​ለ​ሁና አል​ፈር።
21አቤቱ፥ አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና
የዋ​ሃ​ንና ቅኖች ተከ​ተ​ሉኝ።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ከ​ራው ሁሉ ያድ​ነ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in