መዝሙረ ዳዊት 27
27
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ።
ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
2በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥
ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
3ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤
ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ።
4እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤
እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤
ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
5ወደ እግዚአብሔር ሥራ
ወደ እጆቹም ተግባር አላሰቡምና
አፍርሳቸው፥ አትሥራቸውም።
6የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና
እግዚአብሔር ይመስገን።
7እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤
ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤
ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።#ዕብ. “በመዝሙር አመሰግነዋለሁ” ይላል።
8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፥
ለመሲሑ የመድኀኒቱ መታመኛ ነው።
9ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥
ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 27: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 27
27
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ።
ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
2በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥
ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
3ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤
ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ።
4እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤
እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤
ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
5ወደ እግዚአብሔር ሥራ
ወደ እጆቹም ተግባር አላሰቡምና
አፍርሳቸው፥ አትሥራቸውም።
6የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና
እግዚአብሔር ይመስገን።
7እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤
ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤
ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።#ዕብ. “በመዝሙር አመሰግነዋለሁ” ይላል።
8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፥
ለመሲሑ የመድኀኒቱ መታመኛ ነው።
9ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥
ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in