መዝሙረ ዳዊት 29
29
ለቤቱ መመረቅ ምስጋና የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥
የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ” ይላል።
2አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅርም አልኸኝ።
3አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥
ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ለይተህ አዳንኸኝ።
4ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥
ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
5መቅሠፍቱ ከቍጣው ነውና፥#ዕብ. “ለጥቂት ጊዜ” ይላል።
መዳንም ከፈቃዱ#ዕብ. “ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን” ይላል። ነውና፤
ማታ ልቅሶ ይሰማል፥
ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
6እኔም በደስታዬ፥ “ለዘለዓለም አልታወክም” አልሁ።
7አቤቱ፥ በፈቃድህ ለሕይወቴ ኀይልን ስጣት፤
ፊትህን መለስህ፥ እኔም ደነገጥሁ።
8አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
ወደ አምላኬም ለመንሁ።
9ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ?
አፈር ያመሰግንሃልን? ጽድቅህንም ይናገራልን?
10እግዚአብሔር ሰማ፥ ይቅርም አለኝ፤
እግዚአብሔር ረዳቴ ሆነኝ።
11ልቅሶዬን መልሰህ ደስ አሰኘኸኝ።
ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ።
12ክብሬ እንዲዘምርልህ እንዳልደነግጥም፥#ዕብ. “ዝም እንዳልልም” ይላል።
አቤቱ፥ አምላኬ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 29: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 29
29
ለቤቱ መመረቅ ምስጋና የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥
የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ” ይላል።
2አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅርም አልኸኝ።
3አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥
ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ለይተህ አዳንኸኝ።
4ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥
ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
5መቅሠፍቱ ከቍጣው ነውና፥#ዕብ. “ለጥቂት ጊዜ” ይላል።
መዳንም ከፈቃዱ#ዕብ. “ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን” ይላል። ነውና፤
ማታ ልቅሶ ይሰማል፥
ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
6እኔም በደስታዬ፥ “ለዘለዓለም አልታወክም” አልሁ።
7አቤቱ፥ በፈቃድህ ለሕይወቴ ኀይልን ስጣት፤
ፊትህን መለስህ፥ እኔም ደነገጥሁ።
8አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
ወደ አምላኬም ለመንሁ።
9ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ?
አፈር ያመሰግንሃልን? ጽድቅህንም ይናገራልን?
10እግዚአብሔር ሰማ፥ ይቅርም አለኝ፤
እግዚአብሔር ረዳቴ ሆነኝ።
11ልቅሶዬን መልሰህ ደስ አሰኘኸኝ።
ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ።
12ክብሬ እንዲዘምርልህ እንዳልደነግጥም፥#ዕብ. “ዝም እንዳልልም” ይላል።
አቤቱ፥ አምላኬ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in