መዝሙረ ዳዊት 33
33
ባሳደደው በአቤሜሌክ ፊት መልኩን በለወጠ ጊዜ፥ በሄደም ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ።
ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።
2ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥
ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው።
3እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት፥
በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
4እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥
ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥
ፊታችሁም አያፍርም።
6ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥
ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ
ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
8እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወቁም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እዩ” ይላል።
በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
9ለሚፈሩት ችግር የለባቸውምና
ቅዱሳን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
10ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥
እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አልተቸገሩም።
11ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤
እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችሁ ዘንድ፤
12ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው?
በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው?
13አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥
ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
14ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤
ሰላምን ሻት፥ ተከተላትም።
15የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃኑ፥
ጆሮቹም ወደ ልመናቸው ናቸውና።
16መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ
የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው።
17ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው፥
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
18እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥
በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል።
19የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥
እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።
20እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥
ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
21የኃጥእ ሞቱ ክፉ ነው
ጽድቅንም#ዕብ. “ጻድቃንን” ይላል። የሚጠሉ ይጸጸታሉ።
22የባሪያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል፥
በእርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 33: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 33
33
ባሳደደው በአቤሜሌክ ፊት መልኩን በለወጠ ጊዜ፥ በሄደም ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ።
ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።
2ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥
ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው።
3እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት፥
በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
4እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥
ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥
ፊታችሁም አያፍርም።
6ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥
ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ
ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
8እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወቁም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እዩ” ይላል።
በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
9ለሚፈሩት ችግር የለባቸውምና
ቅዱሳን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
10ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥
እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አልተቸገሩም።
11ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤
እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችሁ ዘንድ፤
12ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው?
በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው?
13አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥
ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
14ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤
ሰላምን ሻት፥ ተከተላትም።
15የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃኑ፥
ጆሮቹም ወደ ልመናቸው ናቸውና።
16መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ
የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው።
17ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው፥
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
18እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥
በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል።
19የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥
እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።
20እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥
ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
21የኃጥእ ሞቱ ክፉ ነው
ጽድቅንም#ዕብ. “ጻድቃንን” ይላል። የሚጠሉ ይጸጸታሉ።
22የባሪያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል፥
በእርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in