YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 7

7
ስለ ብን​ያ​ማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​መ​ረው የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በአ​ንተ ታመ​ንሁ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፤
ከሚ​ከ​ብ​ቡኝ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱኝ” ይላል። ሁሉ አድ​ነ​ኝና አው​ጣኝ፥
2ነፍ​ሴን እንደ አን​በሳ እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት፥
የሚ​ያ​ድ​ንና የሚ​ታ​ደግ ሳይ​ኖር።
3አቤቱ አም​ላኬ፥ እን​ዲ​ህስ ካደ​ረ​ግሁ፥
ዐመ​ፃም በእጄ ቢኖር፥
4ክፉ ላደ​ረ​ጉ​ብ​ኝም ክፉን መል​ሼ​ላ​ቸው ብሆን፥
ጠላ​ቶቼ ዕራ​ቁ​ቴን ይጣ​ሉኝ።
5ጠላት ነፍ​ሴን ያሳ​ድ​ዳት፤ ያግ​ኛ​ትም፥
ሕይ​ወ​ቴን በም​ድር ላይ ይር​ገ​ጣት፤
ክብ​ሬ​ንም በት​ቢያ ላይ ያዋ​ር​ደው።
6አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ ተነሥ፤
በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤
አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ባዘ​ዝ​ኸው ሥር​ዐት ተነሥ።
7የአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይከ​ብ​ብ​ሃል፤
ስለ​ዚ​ህም ወደ አር​ያም ተመ​ለስ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤
አቤቱ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ጽድቄ” ይላል። ፍረ​ድ​ልኝ፤
እንደ የዋ​ህ​ነ​ቴም ይሁ​ን​ልኝ።
9የኃ​ጥ​ኣን ክፋት ያል​ቃል፥
ጻድ​ቃ​ንን#ግሪክ ሰባ. ሊ. በነ​ጠላ። ግን ታቃ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ይረ​ዳ​ኛል#ዕብ. “የጽ​ድቅ ጋሻዬ ነው” ይላል።
ልበ ቅኖ​ችን የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው እርሱ ነው።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ው​ነት ዳኛ ነው፤
ኀይ​ለ​ኛም ታጋ​ሽም ነው፤
ሁል​ጊ​ዜም ጥፋ​ትን አያ​መ​ጣም።
12ባት​መ​ለሱ ግን ሰይ​ፉን ይመ​ዝ​ዛል፥#ዕብ. “ይስ​ላል” ይላል።
ቀስ​ቱን ገተረ አዘ​ጋ​ጀም፤
13የሚ​ገ​ድል መር​ዝ​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞት መሣ​ሪ​ያን” ይላል። አዘ​ጋ​ጀ​በት፤
ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ቃ​ጠሉ አደ​ረገ።
14እነሆ፥ ዐመ​ፀኛ በዐ​መፁ ተጨ​ነቀ፤
ጭን​ቅን ፀነሰ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ወለደ።
15ጕድ​ጓ​ድ​ንም ማሰ፥ ቈፈ​ረም።
ባደ​ረ​ገ​ውም ጕድ​ጓድ ይወ​ድ​ቃል።
16ጉዳቱ በራሱ ይመ​ለ​ሳል፥
ዐመ​ፃ​ውም በአ​ናቱ ላይ ትወ​ር​ዳ​ለች።
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ጽድቁ መጠን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥
ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም እዘ​ም​ራ​ለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in