YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 82

82
የአ​ሳፍ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?
አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።
2እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ጮኸ​ዋ​ልና፥
ጠላ​ቶ​ች​ህም ራሳ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተ​ዋ​ልና።
3ሕዝ​ብ​ህን በም​ክር ሸነ​ገ​ሉ​አ​ቸው፥
በቅ​ዱ​ሳ​ን​ህም ላይ ተማ​ከሩ።
4“ኑ ከሕ​ዝብ ለይ​ተን እና​ጥ​ፋ​ቸው፥
ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ስም አያ​ስቡ” አሉ።
5በአ​ን​ድ​ነት ተካ​ክ​ለው ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፤
በአ​ንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤
ቃል ኪዳ​ንም አደ​ረጉ፤
6የኤ​ዶ​ም​ያስ ወገ​ኖች፥ እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም፥
ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንም፥
7ጌባል፥ አሞ​ንም፥ አማ​ሌ​ቅም፥
ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከጢ​ሮስ ሰዎች ጋር፤
8አሦ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተባ​በረ፥
ለሎጥ ልጆ​ችም ረዳት ሆኑ​አ​ቸው።
9እንደ ምድ​ያ​ምና እንደ ሲሣራ፥
በቂ​ሶ​ንም ወንዝ እንደ ኢያ​ቢስ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።
10እንደ ዕን​ዶር ሰዎች ይጥፉ
እንደ ምድር ትቢያ ይሁኑ።
11አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ሔሬ​ብና እንደ ዜብ፥
ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እንደ ዛብ​ሄ​ልና እንደ ስል​ማና አድ​ር​ጋ​ቸው።
12የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ እን​ወ​ር​ሳ​ለን የሚ​ሉ​ትን።
13አም​ላኬ ሆይ፥ እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር፥
በእ​ሳት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በነ​ፋስ ፊት” ይላል። ፊትም እንደ አለ ገለባ አድ​ር​ጋ​ቸው።
14እሳት ዱርን እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል፥
ነበ​ል​ባ​ልም ተራ​ሮ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ፥
15እን​ዲሁ በቍ​ጣህ አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥
በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸው።
16በፊ​ታ​ቸው እፍ​ረ​ትን ሙላ፥
አቤቱ፥ ስም​ህን ይወቁ።#ዕብ. “ይፈ​ልጉ” ይላል።
17ይፈሩ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ይታ​ወኩ፤
ይጐ​ስ​ቍሉ፥ ይጥ​ፉም።
18ስም​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ፥
በም​ድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Free Reading Plans and Devotionals related to መዝ​ሙረ ዳዊት 82

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy