መጽሐፈ ተግሣጽ 6
6
1 # በዕብራይስጥ ምዕ. 31 ከቍ. 10 እስከ 31 ያለው ነው። ልባም ሴትን ማን ያገኛታል?
ዋጋው ብዙ ከሆነ ከከበረ ዕንቍ እጅግ የከበረች ናት።
2እንደዚህ ባለችዋ ሴት የባልዋ ልብ ይታመንባታል፥
እንዲህ ያለችው ሴትም ከመልካም ምርኮ አታሳንሰውም።
3ዕድሜዋን ሙሉ በክፉ ላይ ክፉ ያይደለ፥
በበጎ ላይ በጎ እየሠራች ባሏን ትረዳዋለች።
4የበግ ጠጕርንና የተልባ እግርን እያባዘተች፥
በእጆችዋ መልካም ትሠራለች።
5እርስዋ ከሩቅ እንደምትነግድ፥
ሀብትንም ሁሉ እንደምትሰበስብ መርከብ ናት፤
6ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች፤
ለቤተ ሰዎችዋ ምግባቸውን ትሰጣለች።
ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች።
7እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች፤
ከእጅዋም ፍሬ ወይንን ትተክላለች።
8ወገብዋንም በኀይል ትታጠቃለች፥
እጆችዋንም ለሥራ ታወጣለች።
9ሥራ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች፤
መብራቷ ሌሊቱን ሁሉ አይጠፋም።
10እጆችዋንም ወደሚጠቅም ሥራ ትዘረጋለች፥
ክንድዋንም ለመፍተል ታበረታለች።
11እጅዋን ለችግረኛ ትዘረጋለች፥
መሀል እጅዋንም ወደ ድሃ ትዘረጋለች።
12ባሏ በውጭ የዘገየ እንደ ሆነ በቤት ስላሉት ምንም አያስብም ።
ቤተ ሰዎችዋ ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና።
13ለባሏ እጥፍ ሆኖ ከተፈተለ የተልባ እግር መጐናጸፊያ ትሠራለች፤
ለራስዋም ከነጭ ሐር ልብስን ትሠራለች።
14ባልዋ በሀገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ፥
በአደባባይ የታወቀ ይሆናል።
15የበፍታ ቀሚስ እየሠራች ትሸጣለች።
ለከነዓናውያንም ድግ ትሸጣለች።
ሕጋዊ በሆነ ነገር አፍዋን ትከፍታለች፤
ለአንደበቷም መጠንን ታደርጋለች።
16ብርታትንና ውበትን ትለብሳለች፤
በኋላም ዘመን ላይ ደስ ይላታል።
17ወደ ቤትዋ የሚገባ ብዙ ነው፥
የስንፍና እንጀራንም አትበላም።
18ሕግና ምጽዋት በአፍዋ አለ፥
አፍዋን በጥበብና ሕግ ባለው ሥርዐት ትከፍታለች።
19ምጽዋቷ ልጆችዋን ያሳድጋል፥ ያበለጥጋልም፤
ባልዋም እንዲህ ሲል ያመሰግናታል፦
20“ብዙ ሴቶች ልጆች ሀብትን ሰበሰቡ፤
ብዙዎቹም ኀይልን አደረጉ፤
አንቺ ግን ትበልጫለሽ፥ ከሁሉም ትልቂያለሽ።”
21ውበት ሐሰት ነው፥ ደምግባትም ከንቱ ነው፤
ብልህ ሴት ግን ትባረካለች።
እግዚአብሔርንም የምትፈራ እርስዋ ትመሰገናለች።
22ከከንፈሯ ፍሬ ስጡአት፥
ባሏም በአደባባይ ይመሰገናል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ተግሣጽ 6: አማ2000
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፈ ተግሣጽ 6
6
1 # በዕብራይስጥ ምዕ. 31 ከቍ. 10 እስከ 31 ያለው ነው። ልባም ሴትን ማን ያገኛታል?
ዋጋው ብዙ ከሆነ ከከበረ ዕንቍ እጅግ የከበረች ናት።
2እንደዚህ ባለችዋ ሴት የባልዋ ልብ ይታመንባታል፥
እንዲህ ያለችው ሴትም ከመልካም ምርኮ አታሳንሰውም።
3ዕድሜዋን ሙሉ በክፉ ላይ ክፉ ያይደለ፥
በበጎ ላይ በጎ እየሠራች ባሏን ትረዳዋለች።
4የበግ ጠጕርንና የተልባ እግርን እያባዘተች፥
በእጆችዋ መልካም ትሠራለች።
5እርስዋ ከሩቅ እንደምትነግድ፥
ሀብትንም ሁሉ እንደምትሰበስብ መርከብ ናት፤
6ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች፤
ለቤተ ሰዎችዋ ምግባቸውን ትሰጣለች።
ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች።
7እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች፤
ከእጅዋም ፍሬ ወይንን ትተክላለች።
8ወገብዋንም በኀይል ትታጠቃለች፥
እጆችዋንም ለሥራ ታወጣለች።
9ሥራ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች፤
መብራቷ ሌሊቱን ሁሉ አይጠፋም።
10እጆችዋንም ወደሚጠቅም ሥራ ትዘረጋለች፥
ክንድዋንም ለመፍተል ታበረታለች።
11እጅዋን ለችግረኛ ትዘረጋለች፥
መሀል እጅዋንም ወደ ድሃ ትዘረጋለች።
12ባሏ በውጭ የዘገየ እንደ ሆነ በቤት ስላሉት ምንም አያስብም ።
ቤተ ሰዎችዋ ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና።
13ለባሏ እጥፍ ሆኖ ከተፈተለ የተልባ እግር መጐናጸፊያ ትሠራለች፤
ለራስዋም ከነጭ ሐር ልብስን ትሠራለች።
14ባልዋ በሀገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ፥
በአደባባይ የታወቀ ይሆናል።
15የበፍታ ቀሚስ እየሠራች ትሸጣለች።
ለከነዓናውያንም ድግ ትሸጣለች።
ሕጋዊ በሆነ ነገር አፍዋን ትከፍታለች፤
ለአንደበቷም መጠንን ታደርጋለች።
16ብርታትንና ውበትን ትለብሳለች፤
በኋላም ዘመን ላይ ደስ ይላታል።
17ወደ ቤትዋ የሚገባ ብዙ ነው፥
የስንፍና እንጀራንም አትበላም።
18ሕግና ምጽዋት በአፍዋ አለ፥
አፍዋን በጥበብና ሕግ ባለው ሥርዐት ትከፍታለች።
19ምጽዋቷ ልጆችዋን ያሳድጋል፥ ያበለጥጋልም፤
ባልዋም እንዲህ ሲል ያመሰግናታል፦
20“ብዙ ሴቶች ልጆች ሀብትን ሰበሰቡ፤
ብዙዎቹም ኀይልን አደረጉ፤
አንቺ ግን ትበልጫለሽ፥ ከሁሉም ትልቂያለሽ።”
21ውበት ሐሰት ነው፥ ደምግባትም ከንቱ ነው፤
ብልህ ሴት ግን ትባረካለች።
እግዚአብሔርንም የምትፈራ እርስዋ ትመሰገናለች።
22ከከንፈሯ ፍሬ ስጡአት፥
ባሏም በአደባባይ ይመሰገናል።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in