YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 16

16
1ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የም​ት​ላ​ላ​ከ​ውን እኅ​ታ​ች​ንን ፌቤ​ንን አደራ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ 2ለቅ​ዱ​ሳ​ንም እን​ደ​ሚ​ገባ በጌ​ታ​ችን ተቀ​በ​ሉ​አት፤ እር​ስዋ ለብ​ዙ​ዎች፥ ለእ​ኔም ረዳት ናትና፤ ለች​ግ​ራ​ች​ሁም በፈ​ቀ​ዳ​ች​ሁት ቦታ መድ​ቡ​አት።#ግሪኩ እና አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ከእ​ና​ንተ በም​ት​ፈ​ል​ገው በማ​ን​ና​ውም ነገር ርዱ​አት” ይላል።
3 # የሐዋ. 18፥2። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሥራ ከእኔ ጋር የተ​ባ​በ​ሩ​ትን ጵር​ስ​ቅ​ላ​ንና አቂ​ላን ሰላም በሉ፤ 4ስለ እኔ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለመ​ከራ አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የማ​መ​ሰ​ግ​ና​ቸ​ውም እኔ ብቻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከአ​ሕ​ዛብ ያመኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ቸ​ዋል እንጂ። 5በቤ​ታ​ቸው ያሉ​ትን ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ሰላም በሉ፤ ወዳጄ ኤጴ​ኔ​ጦ​ስ​ንም እን​ዴት ነህ? በሉ፤ ይኸ​ውም በእ​ስያ በክ​ር​ስ​ቶስ ላመኑ ሁሉ መጀ​መ​ሪ​ያ​ቸው ነው። 6ለእ​ና​ንተ ብዙ የደ​ከ​መ​ች​ላ​ች​ሁን ማር​ያ​ም​ንም ሰላም በሉ። 7ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆ​ኑ​ትን ከእኔ ጋር ያመኑ እን​ድ​ራ​ና​ቆ​ስ​ንና ዩል​ያ​ንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ አገ​ለ​ገሉ ሐዋ​ር​ያት ያው​ቁ​አ​ቸ​ዋል። 8በክ​ር​ስ​ቶስ ወን​ድሜ የሆ​ነ​ውን አም​ጵ​ል​ያ​ጦ​ስን ሰላም በሉ። 9የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሥራ በመ​ሥ​ራት የም​ን​ተ​ባ​በ​ረ​ውን ኡሩ​ባ​ኖ​ስን፥ ወዳጄ ስን​ጣ​ክ​ን​ንም ሰላም በሉ። 10በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ኤጤ​ሌ​ንን ሰላም በሉ፤ እነ አር​ስ​ጠ​ቦ​ሎ​ስ​ንም ሰላም በሉ። 11ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆን ሄሮ​ድ​ዮ​ናን ሰላም በሉ፤ በን​ር​ቃ​ሶስ ቤት ያሉ​ት​ንና በክ​ር​ስ​ቶስ ያመ​ኑ​ትን ምእ​መ​ናን ሰላም በሉ። 12በጌ​ታ​ችን ስም መከራ የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ና​ንና የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ስን ወገ​ኖች ሰላም በሉ። በጌ​ታ​ችን ስም ብዙ የደ​ከ​መች እኅ​ታ​ች​ንን ጠር​ሴ​ዳን ሰላም በሉ። 13#ማር. 15፥21። ጌታ​ችን የመ​ረ​ጠው ሩፎ​ንን፥ እና​ቱ​ንም፥ ለእ​ኔም እናቴ የሆ​ነ​ች​ውን ሰላም በሉ። 14አስ​ቀ​ሪ​ጦ​ስን፥ አል​ሶ​ን​ጳን፥ ሄር​ሜ​ስን፥ ጳጥ​ሮ​ባ​ስን፥ ሄር​ማ​ስን፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ን​ንም ሰላም በሉ። 15ፊሎ​ሎ​ጎ​ስን፥ ዩል​ያን፥ ኔር​ዮ​ስን፥ እኅ​ቱ​ንም አሊ​ን​ጳ​ስን ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን ሁሉ ሰላም በሉ። 16እርስ በር​ሳ​ችሁ በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ ሰላም ተባ​ባሉ፤ የክ​ር​ስ​ቶስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል።
17ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እና​ንተ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን ትም​ህ​ርት የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትን፥ መለ​ያ​የ​ት​ንና ማሰ​ና​ከ​ያን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን እን​ድ​ታ​ው​ቁ​ባ​ቸው እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ 18እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤ 19መታ​ዘ​ዛ​ች​ሁም በሁሉ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል፤ እኔም በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ናል፤ ለመ​ል​ካም ነገር ጠቢ​ባን፥ ለክፉ ነገ​ርም የዋ​ሃን እን​ድ​ት​ሆኑ እፈ​ል​ጋ​ለሁ። 20የሰ​ላም አም​ላ​ክም ፈጥኖ ሰይ​ጣ​ንን ከእ​ግ​ራ​ችሁ በታች ይቀ​ጥ​ቅ​ጠው፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
21 # የሐዋ. 16፥1። ከእኔ ጋር በሥራ የሚ​ተ​ባ​በ​ረው ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ ከዘ​መ​ዶች ወገን የሚ​ሆኑ ሉቅ​ዮ​ስም፥ ኢያ​ሶ​ንም፥ ሱሲ ጴጥ​ሮ​ስም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል። 22ይህ​ችን መል​እ​ክት የጻ​ፍ​ኋት እኔ ጤር​ጥ​ዮስ በጌ​ታ​ችን ስም ሰላም እላ​ች​ኋ​ለሁ። 23#የሐዋ. 19፥29፤ 1ቆሮ. 1፥14፤ 2ጢሞ. 4፥20። እኔ​ንና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ሁሉ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​በለ ጋይ​ዮ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ የከ​ተ​ማው መጋቢ አር​ስ​ጦ​ስና ወን​ድ​ማ​ችን ቁአ​ስ​ጥ​ሮ​ስም ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል። 24ከዓ​ለም አስ​ቀ​ድሞ ምሥ​ጢሩ ተሰ​ውሮ ስለ ነበረ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​ስ​ተ​ም​ራት ትም​ህ​ርት ላይ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ የሚ​ች​ለው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።
25ይህም በነ​ቢ​ያት ቃልና የዘ​ለ​ዓ​ለም ገዥ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በዚህ ወራት ተገ​ለጠ፤ አሕ​ዛብ ሁሉ ይህን ሰም​ተ​ውና ዐው​ቀው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያምኑ ዘንድ። 26ብቻ​ውን ጠቢብ ለሆ​ነው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይሁን፤ አሜን። 27የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በቆ​ሮ​ን​ቶስ ተጽፋ ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ላ​ላ​ከው በፌ​ቤን እጅ ወደ ሮሜ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy