ወደ ሮሜ ሰዎች 2
2
ወንድሙን ስለሚነቅፍ ሰው
1 #
ማቴ. 7፥1፤ ሉቃ. 6፥37። አንተ ሰው ሆይ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ?#“እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ” የሚለው በግሪኩ የለም። በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠራዋለህና። 2ይህም እንደዚህ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚያመጣ#“... ቅጣትን የሚያመጣ ...” የሚለው በግእዝ ብቻ። የእግዚአብሔር ፍርዱ እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን። 3አንተ ሰው ሆይ፥ በሌላ ላይ አይተህ የምትጠላውንና የምትነቅፈውን ያን አንተ ራስህ የምትሠራው ከሆነ፥ ከእግዚአብሔር ፍርድ እንደምታመልጥ ታስባለህን? 4ወይስ በቸርነቱ ብዛት በመታገሡ፥ ለአንተም እሺ በማለቱ እግዚአብሔርን አላዋቂ ልታደርገው ታስባለህን? የእግዚአብሔርስ ቸርነቱ አንተን ወደ ንስሓ እንዲመልስህ አታውቅምን? 5ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ። 6#መዝ. 61፥12፤ ምሳ. 24፥12። እርሱ በእውነተና ፍርዱ#“... በእውነተና ፍርዱ” የሚለው በግእዝ ብቻ። ለሁሉ እንደ ሥራው ይከፍለዋልና። 7በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል። 8ለሚክዱና እውነትን ለሚለውጡ፥ ዐመፅንም ለሚወድዱ ሰዎች ዋጋቸው ቍጣና መቅሠፍት ነው። 9መከራና ጭንቀት አስቀድሞ በአይሁዳዊ፥ ደግሞም በአረማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው። 10ምስጋናና ክብር፥ ሰላምም አስቀድሞ ለአይሁዳዊ፥ ደግሞም ለአረማዊ፥ ሥራዉ መልካም ለሆነ ሁሉ ነው። 11#ዘዳ. 10፥17። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።
12ከሕግ ወጥተው የበደሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ ያለ ሕግ የበደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈረድባቸዋል። 13በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉ ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ አይጸድቁምና። 14ሕግ የሌላቸው አሕዛብስ እንኳ ለራሳቸው ሕግ ይሠራሉ፤ ራሳቸው ለራሳቸው ሕግን ይደነግጋሉ፤ በሕጋቸው የታዘዘውንም ያደርጋሉ።#ግሪኩ “ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ያደርጋሉ፤ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና” ይላል። 15በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፤ ከሥራቸውም የተነሣ ይታወቃል፤ ሕሊናቸውም ይመሰክርባቸዋል፤ ይፈርድባቸዋልም። 16ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ ሰዎችን በልቡናቸው የሰወሩትንና የሸሸጉትን በሚመረምርበት ጊዜ የሚናገሩትና የሚመልሱት እንደሌለ ስለሚያውቁ ነው።
ራሱ የማይሠራ ለሌላው የሚያስተምር
17አንተ አይሁዳዊ፥ በኦሪትህ የምታርፍ፥ በእግዚአብሔርም የምትመካ ከሆንህ፥ 18ፈቃዱን የምታውቅ፥ መልካሙንም የምትለይ፥ ኦሪትንም የተማርህ ከሆንህ፥ 19አንተ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉት ብርሃን እንደ ሆንህ በራስህ የምትታመን ከሆንህ፥ 20ሰነፎችን ልባሞች የምታደርግ፥ ሕፃናትን የምታስተምር፥ ጻድቅና የምትከብርበትን የኦሪትን ሕግ የምታውቅ የምትመስል፥ 21እንግዲህ ሌላውን የምታስተምር ራስህን እንዴት አታስተምርም? አትስረቁ ትላለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰርቃለህ። 22አታመንዝሩ ትላለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመነዝራለህ፤ ወደ ጐልማሳ ሚስትም ትሄዳለህ፤#“ወደ ጐልማሳ ሚስትም ትሄዳለህ” የሚለው በግሪኩ የለም። ጣዖትን ትጸየፋለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህ። 23በኦሪት ትመካለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ኦሪትን በመሻር እግዚአብሔርን ታቃልለዋለህ። 24#ኢሳ. 52፥5። እንደ ተጻፈም “እነሆ፥ በእናንተ ምክንያት አሕዛብ የእግዚአብሔርን ስም ይሰድባሉ።”
ስለ ግዝረትና ስለ አይሁዳዊነት
25ኦሪትንም ብትፈጽም ግዝረት ትጠቅምሃለች፤ ኦሪትን ባትፈጽም ግን ግዝረትህ አለመገዘር ትሆንብሃለች። 26አንተ ሳትገዘር ብትኖር፥ ኦሪትንም ብትጠብቅ አለመገዘርህ መገዘር ትሆንልሃለች። 27ተገዝረህ ኦሪትን ከምታፈርስ በተፈጥሮ ያገኘሃት አለመገዘርህ አብራህ ብትኖር ይሻልሃል፤#“በተፈጥሮ ያገኘሃት አለመገዘርህ አብራህ ብትኖር ይሻላል” የሚለው በግሪኩ የለም። ኦሪትን ከምታፈርስ ከአንተ ከተገዘርኸው ያ ያልተገዘረው፥ ኦሪትን የሚፈጽመው ይሻላል። 28በውኑ ለሰው ይምሰል አይሁዳዊ መሆን ይገባልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገዘሩአልን? 29#ዘዳ. 30፥6። ዳሩ ግን አይሁዳዊነት በስውር ነው፤ መገዘርም በመንፈስ የልብ መገዘር እንጂ በኦሪት ሥርዐት አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 2: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: