YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 7

7
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! ሕግን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ውሉ እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ሰው በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ሁሉ ሕግ እን​ዲ​ገ​ዛው አታ​ው​ቁ​ምን? 2ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት። 3ስለ​ዚህ ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብት​ሆን አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥ​ታ​ለች፤ ለሌላ ወንድ ብት​ሆ​ንም አመ​ን​ዝራ አት​ባ​ልም።
4ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል። 5የሰ​ውን ሕግ በሠ​ራን ጊዜ ግን በኦ​ሪት ሕግ ደካ​ማ​ነት ቅጣቱ ጸና​ብን፤ ሞት​ንም አፈ​ራን።#ምዕ. 7 ቍ. 5 ከግ​ሪኩ ይለ​ያል። 6አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።
ኦሪ​ትን ስለ መተው
7 # ዘፀ. 20፥17፤ ዘዳ. 5፥21። እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ኦሪት ኀጢ​አት ናትን? አይ​ደ​ለ​ችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባት​ሠራ ኀጢ​አ​ትን ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አት​መኝ” ባትል ኖሮም ምኞ​ትን ፈጽሞ ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር። 8ያችም ትእ​ዛዝ ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት ሆነ​ቻት፤ ምኞ​ት​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ች​ብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳት​ሠራ ኀጢ​አት ሙት ነበ​ረች። 9እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ። 10ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት። 11#ዘፍ. 3፥13። ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ። 12አሁ​ንም ቢሆን ኦሪ​ትስ ቅድ​ስት ናት፤ ትእ​ዛ​ዝ​ዋም ቅዱ​ስና እው​ነት ነው፤ መል​ካ​ምም ነው፤ በረ​ከ​ትም ነው።#“በረ​ከ​ትም ነው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
13እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።#“ኦሪ​ትም መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
ስለ መን​ፈ​ሳዊ ሕግ
14የኦ​ሪት ሕግ መን​ፈ​ሳዊ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ እኔ ግን ለኀ​ጢ​አት የተ​ሸ​ጥሁ ሥጋዊ ነኝ። 15#ገላ. 5፥17። የማ​ደ​ር​ገ​ውን አላ​ው​ቅ​ምና፤ የም​ወ​ደ​ው​ንም ያን ምንም አላ​ደ​ር​ገ​ው​ምና፤ ያንኑ የም​ጠ​ላ​ውን ብቻ እሠ​ራ​ለሁ እንጂ። 16የማ​ል​ወ​ደ​ውን የም​ሠራ ከሆ​ንሁ ግን ያ የኦ​ሪት ሕግ መሠ​ራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስ​ክሩ እኔ ነኝ። 17እን​ግ​ዲ​ያስ በእኔ ላይ ያደ​ረች ኀጢ​አት ናት እንጂ፥ ያን የማ​ደ​ር​ገው እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም። 18በእኔ ማለት በሥ​ጋዬ መል​ካም ነገር እን​ደ​ማ​ይ​ኖር አው​ቃ​ለሁ፤ መል​ካም ሥራ ለመ​ሥ​ራት መሻ​ቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግ​ባር መሥ​ራት ግን የለ​ኝም። 19ያን የም​ወ​ደ​ው​ንም በጎ ነገር የማ​ደ​ርግ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ያን የም​ጠ​ላ​ውን ክፉ​ውን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 20የማ​ል​ወ​ደ​ው​ንስ የም​ሠራ ከሆነ የም​ሠ​ራው እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ በእኔ ላይ ያደ​ረች ኀጢ​አት ናት እንጂ። 21መል​ካም ሥራ እን​ድ​ሠራ የፈ​ቀ​ደ​ል​ኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አም​ጥ​ቶ​ብኝ አገ​ኘ​ሁት። 22በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው። 23ነገር ግን በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለ​ውን ሌላ የኀ​ጢ​አት ሕግ እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ዬም ውስጥ ካለው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጋር ተሰ​ል​ፈው ተዋጉ፤ በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀ​ጢ​አት ሕግም በረ​ታና ወደ እርሱ ማረ​ከኝ። 24እኔ ምንና ወራዳ ሰው ነኝ፤ ከዚህ ሟች ሰው​ነቴ ማን ባዳ​ነኝ? 25በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in