YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ሮሜ ሰዎች 9

9
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን እንደ መረጠ
1በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሐሰ​ትም አል​ና​ገ​ርም። ሕሊ​ና​ዬም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ናል፤ 2በጊ​ዜው ሁሉ ብዙ ኀዘን፥ የማ​ያ​ቋ​ር​ጥም ጭን​ቀት በልቤ አለ። 3በሥጋ ዘመ​ዶ​ችና ወን​ድ​ሞች ስለ​ሚ​ሆኑ እኔ ከክ​ር​ስ​ቶስ እለይ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ። 4#ዘፀ. 9፥4። እና​ህም ልጅ​ነት፥ ክብር፥ ኪዳን፥ ሕግና አም​ልኮ ያላ​ቸው፥ ተስ​ፋም የተ​ሰ​ጣ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ናቸው። 5እነ​ር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ክር​ስ​ቶስ በሥጋ ተወ​ለደ፤ እር​ሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።
6ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አይ​ታ​በ​ልም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን አይ​ደ​ሉ​ምና። 7#ዘፍ. 21፥12። የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ። 8ልጆች እን​ዲ​ሆ​ኑት ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ ከሥጋ የተ​ወ​ለዱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች አይ​ደ​ሉም። 9#ዘፍ. 18፥10። “ከርሞ እንደ ዛሬ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ታገ​ና​ለች፤” ብሎ ተስፋ ሰጥ​ቶ​ታ​ልና። 10ነገር ግን ለእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ርብ​ቃም ለአ​ባ​ታ​ችን ለይ​ስ​ሐቅ መንታ በፀ​ነ​ሰች ጊዜ፥ 11ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥ 12#ዘፍ. 25፥23። እርሱ የጠ​ራው ነው እንጂ ሰው በሥ​ራው የሚ​መ​ረጥ አን​ዳ​ይ​ደ​ለም ያውቁ ዘንድ፥ ለር​ብቃ፥ “ታላቁ ለታ​ናሹ ይገ​ዛል” አላት። 13#ሚል. 1፥2-3። “ያዕ​ቆ​ብን ወደ​ድሁ፤ ዔሳ​ውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አ​ልና። 14እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ላ​ልን? አያ​ደ​ላም። 15#ዘፀ. 33፥19። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ አለው፥ “የም​ም​ረ​ውን እም​ረ​ዋ​ለሁ፤ ይቅር የም​ለ​ው​ንም ይቅር እለ​ዋ​ለሁ።” 16አሁ​ንም ለሮ​ጠና ለቀ​ደመ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ላለው ነው እንጂ። 17#ዘፀ. 9፥16። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለፈ​ር​ዖን በመ​ጽ​ሐፍ እን​ዲህ አለው፥ “ኀይ​ሌን በአ​ንተ ላይ እገ​ልጥ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ይሰማ ዘንድ ስለ​ዚህ አስ​ነ​ሣ​ሁህ።” 18እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።
19እን​ግ​ዲህ ምን ትላ​ለህ? አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትነ​ቅ​ፈ​ዋ​ለ​ህን?#ግሪኩ “እን​ግ​ዲህ እርሱ እስከ አሁን ድረስ ስለ​ምን ይነ​ቅ​ፋል?” ይላል። ምክ​ሩ​ንስ የሚ​ቃ​ወ​ማት አለን?። 20#ኢሳ. 29፥16፤ 45፥9። ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን? 21ሸክላ ሠሪ ከአ​ንድ ጭቃ ግማ​ሹን ለክ​ብር፥ ግማ​ሹ​ንም ለኀ​ሳር አድ​ርጎ ዕቃን ሊሠራ አይ​ች​ል​ምን? 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ሉን የሚ​ገ​ል​ጽ​በ​ትን ቅጣ​ቱን ሊያ​ሳይ ቢወድ፥ ትዕ​ግ​ሥ​ቱን ካሳየ በኋላ ለማ​ጥ​ፋት የተ​ዘ​ጋ​ጁ​ትን ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸ​ውን መላ​እ​ክት#“ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸው መላ​እ​ክት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ “የቍጣ መሣ​ሪ​ያ​ዎች” ይላል። ያመ​ጣል። 23ዳግ​መ​ናም የክ​ብ​ሩን ባለ​ጠ​ግ​ነት ሊያ​ሳይ ቢወድ አስ​ቀ​ድሞ ለወ​ደ​ዳ​ቸ​ውና ለጠ​ራ​ቸው ለይ​ቅ​ርታ የተ​ዘ​ጋጁ የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክ​ትን#“የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ “የም​ሕ​ረት መሣ​ሪ​ያ​ዎች” ይላል። ያመ​ጣል። 24ወደ ክብሩ የጠ​ራ​ንና የሰ​በ​ሰ​በ​ንም እና ነን፤ ነገር ግን ከአ​ሕ​ዛ​ብም ነው እንጂ ከአ​ይ​ሁድ ብቻ አይ​ደ​ለም። 25#ሆሴዕ 2፥23። ነቢዩ ሆሴዕ እን​ዲህ እን​ዳለ “ወገኔ ያል​ነ​በ​ረ​ውን ወገኔ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ወዳጄ ያል​ነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ወዳጄ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። 26#ሆሴዕ 1፥10። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገ​ኖች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም ይባሉ በነ​በ​ሩ​በት ሀገ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ።” 27ኢሳ​ይ​ያ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ስለ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቍጥ​ራ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆ​ንም የተ​ረ​ፉት ይድ​ናሉ። 28#ኢሳ. 10፥22-23። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም ውስጥ ያደ​ር​ገው ዘንድ ያለ​ውን ያለ​ቀና የተ​ቈ​ረጠ ነገ​ርን ይና​ገ​ራ​ልና።” 29#ኢሳ. 1፥9። ኢሳ​ይ​ያ​ስም አስ​ቀ​ድሞ እንደ ተና​ገረ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸባ​ኦት ዘር ያስ​ቀ​ረ​ልን ባይ​ሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞ​ራ​ንም በመ​ሰ​ልን ነበር።”
በእ​ም​ነት ስለ መጽ​ደቅ
30እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ጽድ​ቅን ያል​ፈ​ለ​ጉ​አት አሕ​ዛብ ስንኳ ጽድ​ቅን አገ​ኙ​አት፤ በእ​ም​ነ​ትም ጸደቁ። 31እስ​ራ​ኤል ግን ኦሪ​ትን ሲከ​ተሉ መጽ​ደቅ ተሳ​ና​ቸው፤ የኦ​ሪ​ታ​ቸ​ውን ሥራ አል​ፈ​ጸ​ሙ​ምና።#የኦ​ሪ​ታ​ቸ​ውን ሥራ አል​ፈ​ጸ​ሙም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 32ይህስ ስለ​ምን ነው? ጽድ​ቃ​ቸው የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እንጂ በእ​ም​ነት ስለ አል​ሆነ ነው፤ የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋይ አሰ​ነ​ካ​ከ​ላ​ቸው። 33መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ “በጽ​ዮን የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋ​ይ​ንና የማ​ሰ​ና​ከያ ዐለ​ትን አኖ​ራ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ባ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ወደ ሮሜ ሰዎች 9