YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ጥበብ 1

1
ትክ​ክ​ለኛ ፍር​ድን ስለ መሻት
1የም​ድር ገዥ​ዎች ሆይ፥ ጽድ​ቅን ውደ​ዷት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ኀይል በበጎ ዕው​ቀት አስ​ቡት፥ በቅን ልቡ​ናም ፈል​ጉት። 2በማ​ይ​ፈ​ታ​ተ​ኑት ሰዎች ዘንድ እርሱ ይገ​ኛ​ልና። በማ​ይ​ክ​ዱት ሰዎ​ችም ዘንድ ይገ​ለ​ጣ​ልና። 3ጠማማ አሳብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያር​ቃል፤ የተ​ፈ​ተ​ነ​ችም ኀይል አላ​ዋ​ቂ​ዎ​ችን ትዘ​ል​ፋ​ቸ​ዋ​ለች።
4በተ​ተ​ነ​ኰ​ለች ሰው​ነት ጥበብ አት​ገ​ባ​ምና፤ ለኀ​ጢ​አት በተ​ገዛ ሰው​ነ​ትም አታ​ድ​ር​ምና። 5ተግ​ሣ​ጽን የሚ​ገ​ልጽ መን​ፈስ ቅዱስ ክፉ​ውን ትም​ህ​ርት ያር​ቃ​ልና፥ ከሰ​ነ​ፎ​ችም ልቡና ድል ነሥቶ ይሄ​ዳ​ልና በሚ​መ​ጣም ጊዜ ክፉ​ውን ይዘ​ል​ፈ​ዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለ​ያል። 6ጥበ​ብን የሚ​ገ​ልጽ መን​ፈስ ሰው ወዳጅ ነውና፥ በከ​ን​ፈሩ የሚ​ሳ​ደ​በ​ው​ንም አያ​ነ​ጻ​ውም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ምስ​ክር ነውና፥ ነዋሪ ጕበ​ኛም ልቡ​ና​ውን ይመ​ረ​ም​ረ​ዋል፤ አን​ደ​በ​ቱ​ንም ይሰ​ማ​ዋል። 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ዓለ​ሙን መል​ት​ዋ​ልና። ዓለ​ም​ንም ሁሉ የያ​ዘው እርሱ ነገ​ራ​ቸ​ውን ፈጽሞ ያው​ቃ​ልና። 8ስለ​ዚህ ከሚ​ነ​ገር ከዐ​መፃ ነገ​ራ​ቸው ምንም ከእ​ርሱ አይ​ሰ​ወ​ርም። ሥራ​ውን በመ​ግ​ለጥ ፍርዱ አይ​ተ​ላ​ለ​ፈ​ው​ምና። 9ክፉ​ዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው ምክር ይመ​ረ​ም​ራ​ቸ​ዋ​ልና፥ የነ​ገ​ራ​ቸ​ውም ድምፅ ለበ​ደ​ላ​ቸው ዘለፋ ሊሆ​ን​ባ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ር​ሳ​ልና። 10#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የቅ​ናት ጆሮ ሁሉን ይሰ​ማል” ይላል። ስለ ቅን​አት ሥራ​ውን ሁሉ የሚ​ሰማ አይ​ደ​ለ​ምና፥ የነ​ጐ​ር​ጓ​ርም ድምፅ ከእ​ርሱ አይ​ሰ​ወ​ርም። 11ከማ​ይ​ረባ ነጐ​ር​ጓር ተጠ​በቁ፤ ከሐ​ሜ​ትም አን​ደ​በ​ታ​ች​ሁን ከል​ክሉ፤ በስ​ውር የሚ​ሆን ነገር በከ​ንቱ አይ​ወ​ጣ​ምና፥ የሚ​ወ​ጋና የሚ​ዋሽ አፍ ሰውን ይገ​ድ​ላ​ልና።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሞትን አል​ፈ​ጠ​ረም
12በሕ​ይ​ወ​ታ​ችሁ ስሕ​ተት ለሞት አት​ቅኑ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ጥፋ​ትን አታ​ምጡ። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሞትን አል​ፈ​ጠ​ረ​ምና፤ የሕ​ያ​ዋ​ንም ጥፋት ደስ አያ​ሰ​ኘ​ው​ምና። 14ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥ​ረ​ቱን ፈጥ​ሮ​አ​ልና፥ የዓ​ለም መፈ​ጠ​ርም ለድ​ኅ​ነት ነውና፥ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ የጥ​ፋት መርዝ አል​ነ​በ​ረ​ምና፥ ለሲ​ኦ​ልም በም​ድር ላይ ግዛት አል​ነ​በ​ረ​ው​ምና። 15ጽድቅ አት​ሞ​ት​ምና። 16ክፉ​ዎች ግን በእ​ጃ​ቸ​ውና በቃ​ላ​ቸው ጠሩት፥ ባል​ን​ጀ​ራም አስ​መ​ሰ​ሉት። በእ​ር​ሱም ጠፉ። 17የእ​ርሱ ወገን መሆን ይገ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in