YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ጥበብ 3

3
ቅዱ​ሳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ኤት እን​ደ​ሚ​ጠ​በቁ
1የጻ​ድ​ቃን ነፍስ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ናት፤ መከ​ራም አያ​ገ​ኛ​ቸ​ውም። 2በሰ​ነ​ፎች ዓይ​ኖች ግን የሞቱ መሰሉ፤ በሞ​ትም ከዚህ ዓለም መው​ጣ​ታ​ቸው ክፋት እን​ዳ​ለ​ባ​ቸው ተቈ​ጠረ። 3ሞታ​ቸ​ውም ጥፋት መሰለ፤ እነ​ርሱ ግን በሰ​ላም አሉ። 4በሰው ፊትም ቢፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው ተስ​ፋ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሞት የሌ​ለ​ባት ፍጽ​ምት ሕይ​ወት ናት።
5ጥቂት መከራ ተቀ​ብ​ለው ብዙ ክብር ያገ​ኛሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈት​ኗ​ቸው ለእ​ርሱ የተ​ገቡ ሆነው አግ​ኝ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ልና። 6ወርቅ በከ​ውር እን​ዲ​ፈ​ተን ፈተ​ና​ቸው፤ እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው። 7በሚ​ጐ​በ​ኙ​በ​ትም ወራት እንደ ፀሐይ ያበ​ራሉ፤ በብ​ርዕ ላይ የወ​ደቀ የእ​ሳት ፍን​ጣሪ እን​ዲ​ሰፋ በክ​ብር እየ​ሰፉ ይሄ​ዳሉ። 8አሕ​ዛ​ብን ይገ​ዛሉ፤ በሕ​ዝ​ብም ላይ ይሠ​ለ​ጥ​ናሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይነ​ግ​ሥ​ላ​ቸ​ዋል። 9በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምኑ ሰዎች እው​ነ​ትን ያው​ቃሉ፤ ጸጋና ምሕ​ረት ለመ​ረ​ጣ​ቸው ነውና፥ የተ​ገ​ለጠ ጕብ​ኝ​ቱም ለጻ​ድ​ቃኑ ነውና ምእ​መ​ናን በእ​ርሱ ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ።
ክፉ​ዎች በክ​ፋ​ታ​ቸው እን​ደ​ሚ​ጐዱ
10ክፉ​ዎች ሰዎች ግን እን​ዳ​ሰቡ ክፉ ፍር​ድን ያገ​ኛሉ፥ እው​ነ​ት​ንም ያቀ​ለሉ ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቁ።
11ጥበ​ብ​ንና ተግ​ሣ​ጽን የሚ​ንቁ ሰዎች ጐስ​ቋ​ሎች ናቸው፤ አለ​ኝ​ታ​ቸው ከንቱ ነው፤ ድካ​ማ​ቸ​ውም፥ መከ​ራ​ቸ​ውም ጥቅም የሌ​ለው ነው፤ ሥራ​ቸ​ውም ከንቱ ነው፤ 12ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሰነ​ፎች ናቸው፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ጠማ​ሞች ናቸው፤ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም የተ​ረ​ገመ ነው።
በን​ጽ​ሕና ስለ​መ​ኖር
13ነውር የሌ​ለ​ባት፥ የኀ​ጢ​አት ምን​ጣፍ የማ​ታ​ውቅ መካን ሴት ብፅ​ዕት ናት፥ ከኀ​ጢ​አ​ትም የነ​ጻች ናት፥ ይህች እን​ዲህ ያለ​ችው ሴት ነፍ​ሳት በሚ​ጐ​በ​ኙ​በት ጊዜ ፍሬ ታገ​ኛ​ለች። 14የተ​መ​ረ​ጠች የሃ​ይ​ማ​ኖት ዋጋ ትሰ​ጠ​ዋ​ለ​ችና፥ በሚ​ወ​ደድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ዕድሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና በእጁ በደ​ልን ያል​ሠራ፥ በእ​ግ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ክፉ ነገ​ርን ያላ​ሰበ ጃን​ደ​ረ​ባም ብፁዕ ነው። 15የደግ ሰው የድ​ካሙ ፍሬ ክብ​ርና ጌጥ ነው፤ ለዕ​ው​ቀ​ቱም ሥር ውድ​ቀት የለ​በ​ትም።
16ያመ​ን​ዝ​ራ​ዎች ልጆች ግን ከቍ​ጥር የጐ​ደሉ ይሆ​ናሉ። ከሕግ ተላ​ላፊ መኝታ የተ​ወ​ለደ ልጅም ይጠ​ፋል። 17ኑሮ​አ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ ቢበዛ ምንም አይ​ቈ​ጠ​ርም፤ ሽም​ግ​ል​ና​ቸ​ውም በፍ​ጻ​ሜ​ያ​ቸው የጐ​ሰ​ቈለ ይሆ​ናል። 18ፈጥ​ነ​ውም ቢሞቱ በፍ​ርድ ቀን ተስ​ፋና መጽ​ና​ናት አይ​ኖ​ራ​ቸ​ውም። 19ለዐ​መ​ፀኛ ትው​ልድ ፍጻ​ሜዋ ክፉ ነውና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in