YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ኢሳይያስ 12

12
1በዚያም ቀን፦ አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኽኛልምና አመሰግንሃለሁ። 2እነሆ፥ አምላክ መድሃኒቴ ነው፥ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ። 3ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። 4በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፥ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፥ ስሙ ከፍ ያለ እንደሆነ ተናገሩ። 5ታላቅ ሥራ ሰርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ። 6አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in