1
የዮሐንስ ወንጌል 19:30
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ጌታችን ኢየሱስም ሆምጣጤውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈጸመ” አለ፤ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን ሰጠ።
Compara
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:30
2
የዮሐንስ ወንጌል 19:28
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ባየ ጊዜ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:28
3
የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
ጌታችን ኢየሱስም እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙሩን ቆመው ባያቸው ጊዜ እናቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት። ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ “እናትህ እነኋት” አለው፤ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ተቀብሎ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:26-27
4
የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
ወደ ጌታችን ኢየሱስም ሄደው ፈጽሞ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ የቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ያንጊዜም ከእርሱ ደምና ውኃ ወጣ።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:33-34
5
የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
ይህ ሁሉ የሆነው “ከእርሱ ዐፅሙን አትስበሩ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። ሌላዉም መጽሐፍ ደግሞ“ የወጉትን ያዩታል” ይላል።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:36-37
6
የዮሐንስ ወንጌል 19:17
መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:17
7
የዮሐንስ ወንጌል 19:2
ጭፍሮችም የእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም አለበሱት።
Explorar የዮሐንስ ወንጌል 19:2
Inici
La Bíblia
Plans
Vídeos