የዮሐንስ ወንጌል 2

2
የገሊላው ቃና ሰርግ
1በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ 2ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። 3የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፤” አለችው። 4ኢየሱስም “አንቺ ሴት ሆይ#2፥4 ሰው እናቱን “አንቺ ሴት”፥ ማለቱ ያልተለመደ ወይም የሚያስገርም ነው። ክብርን የሚቀንስ እንዳልሆነ ግን ከማቴ፥ 15፥28 ዮሐ.8፥10 ዮሐ. 19፥26 ዮሐ 20፥13 ዮሐ 20፥15 ማየት ይቻላል። ሐሳቡ “እመቤት ሆይ” ወይም “የእኔ እመቤት” እንደ ማለት ነው።፦ ይህ ጉዳይ ለእኔ ምንድነው?#2፥4 “ይህ ጉዳይ ለእኔና ለአንቺ ምንድነው?” የሚል ትርጒም ሊኖረው ይችላል። እንደዚሁም “በእኔና በአንቺ መካከል ምን?” የሚል ትርጒም ሊያሰማ ይችላል። የዚህን የኢየሱስ ጥያቄ መረዳት ቀላል አይደለም። ኢየሱስ በይፋ አገልግሎቱን በመጀመሩ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን ያሳያል። የብሉይ ኪዳንን የመንጻት ውሃ ወደ ወይን ሲቀይረው ኢየሱስ የመሢሕን ዘመን መምጣት የሚያበስረው የአዲስ ኪዳን ምሽራ መሆኑን ያመለክታል። ይልቁንም በእናትና በልጅ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ፥ “ሴት” በሚለው ቃል አማካኝነት ተጨማሪ ተምሳሌታዊ ትርጒም እንዳለው ይገልጻል። በኢየሱስና በማርያም መካከል ግንኙነት እንደሌለ ግን አያመለክትም። ጊዜዬ ገና አልደረሰም#2፥4 “ጊዜዬ ወይም ሰዓቴ አልደረሰምን?” ብለው የሚተረጉሙም አሉ።፤” አላት። 5እናቱም ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፤” አለቻቸው። 6አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። 7ኢየሱስም “ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው፤” አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። 8“አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት፤” አላቸው፤ ሰጡትም። 9አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ 10“ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፤” አለው። 11ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን እንደ አነጻ
(ማቴ. 21፥12-43ማር. 11፥15-17ሉቃ. 19፥45-46)
12 # ማቴ. 4፥13። ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ለጥቂት ቀን ተቀመጡ።
13 # ዘፀ. 12፥1-27። የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 14በመቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና እርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ 15የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤ 16እርግብ ሻጪዎችንም “ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት፤” አላቸው። 17#መዝ. 68፥10።ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። 18ስለዚህ አይሁድ መልሰው “ይህንን ስለ ማድረግህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። 19#ማቴ. 26፥61፤ 27፥40፤ ማር. 14፥58፤ 15፥29።ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ፤” አላቸው። 20ስለዚህ አይሁድ “ይህ ቤተ መቅደስ ለአርባ ስድስት ዓመት እየተሠራ ነበር፤ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን?” አሉት። 21እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ እየተናገረ ነበር። 22ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
23በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳሉ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤ 24ነገር ግን ኢየሱስ በበኩሉ አይተማመንባቸውም ነበር፤ 25ስለ ሰው ማንም እንዲመሰክር አያስፈልገውም ነበር፤ በሰው ውስጥ ያለውን እራሱ ያውቅ ነበርና።

Subratllat

Comparteix

Copia

None

Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió