የዮሐንስ ወንጌል 14
14
ስለ እምነት
1“ልባችሁ አይደንግጥ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ። 2በአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያና ማረፊያ#“ማረፊያ” የሚለው በግሪኩ የለም። አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ቦታ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበር። 3ከሄድሁና ቦታ ካዘጋጀሁላችሁም ዳግመኛ እመጣለሁ፤ እናንተም እኔ በአለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ። 4ወዴትም እንደምሄድ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ መንገዱንም ታውቃላችሁ።” 5ቶማስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የምትሄድበትን የማናውቅ እንግዲህ መንገዱን እንዴት እናውቃለን?” አለው። 6ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ#በግሪኩ “እኔ መንገድ፥ እውነትና ሕይወትም ነኝ” ይላል። እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። 7እኔንስ ብታውቁኝ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን አውቃችሁታል፤ አይታችሁትማል።”
8ፊልጶስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። 9ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብሬአችሁ ስኖር አታወቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እንግዲህ እንዴት አብን አሳየን ትላለህ? 10እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁ ይህ ቃልም ከራሴ የተናገርሁት አይደለም፤ በእኔ ያለ አብ እርሱ ይህን ሥራ ይሠራዋል እንጂ። 11እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ እመኑ፤ ያለዚያም ስለ ሥራዬ እመኑኝ።
12“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና። 13አብ በወልድ ይከብር ዘንድ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። 14በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ያን አደርግላችኋለሁ።
ስለ ጰራቅሊጦስ
15“ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ። 16እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ ይልክላችኋል። 17እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ይኖራልና፤ ያድርባችሁማልና።
18“የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንግዲህ ወዲህም ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ። 20እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ፥#“አብ በእኔ እንደ አለ” የሚለው በግሪኩ የለም። እናንተም በእኔ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ። 21ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለ የሚጠብቀውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” 22የአስቆሮቱ ሰው ያይደለ ይሁዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ያይደለ ለእኛ ራስህን ትገልጥ ዘንድ እንዳለህ የተናገርኸው ምንድን ነው?” አለው። 23ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አለው፥ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ ወደ እርሱም መጥተን በእርሱ ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን። 24የማይወደኝ ግን ቃሌን አይጠብቅም፤ ይህም የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ቃል ነው እንጂ የእኔ ቃል አይደለም።
25“ከእናንተም ጋር ሳለሁ ይህን ነገርኋችሁ። 26ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው#በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “መንፈስ ቅዱስ” ይላል። የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።
ስለ ሰላም
27“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም። 28እኔ እንደምሄድ ወደ እናንተም እንደምመለስ የነገርኋችሁን ሰምታችኋል፤ ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበልጠኛልና። 29አሁንም ይህ በሆነ ጊዜ ታምኑ ዘንድ አስቀድሜ ሳይሆን ነገርኋችሁ። 30እንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፤ የዚህ ዓለም ገዢ ይመጣልና፤ በእኔም ላይ ምንም አያገኝም። 31ነገር ግን አብን እንደምወደው ዓለም ያውቅ ዘንድ አብ ትእዛዙን እንደ ሰጠኝ እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ተነሡ ከዚህ፤ እንሂድ።
S'ha seleccionat:
የዮሐንስ ወንጌል 14: አማ2000
Subratllat
Comparteix
Copia
Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió

: