የዮሐንስ ወንጌል 8
8
ስለ አመንዝራዪቱ ሴት ፍርድ
1ጌታችን ኢየሱስም ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። 2በጥዋትም ገስግሦ ዳግመኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ እርሱም ተቀምጦ ያስተምራቸው ጀመር። 3ጻፎችና ፈሪሳውያንም በዝሙት የተያዘች ሴት ወደ እርሱ አምጥተው በመካከል አቆሙአት። 4እንዲህም አሉት፥ “መምህር ሆይ፥ ይቺን ሴት ስታመነዝር አግኝተን ያዝናት። 5#ዘሌ. 20፥10፤ ዘዳ. 22፥22-24። እንደዚችም ያለችው በድንጋይ እንድትደበደብ ሙሴ በኦሪት አዘዘን፤ እንግዲህ አንተ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” 6በእርሱም ላይ ምክንያት ሊያገኙ ሲፈትኑት ይህን አሉ፤ ጌታችን ኢየሱስም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። 7ብዙ ጊዜ መላልሰው በጠየቁት ጊዜም ዐይኖቹን አንሥቶ፥ “ከእናንተ ኀጢኣት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት” አላቸው። 8ዳግመኛም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። 9እነርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊናቸው ወቅሶአቸው ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ድረስ፥ አንዳንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴትዮዪቱም በመካከል ቆማ ነበር። 10ጌታችን ኢየሱስም ቀና ብሎ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚከሱሽ ወዴት አሉ?” 11እርስዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማየው የለም” ብላ መለሰችለት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ ኀጢኣት አትሥሪ” አላት።
ኢየሱስ የዓለም ብርሃን
12 #
ማቴ. 5፥14፤ ዮሐ. 9፥5። ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው። 13#ዮሐ. 5፥31። ፈሪሳውያንም፥ “አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህ፤ እንግዲያስ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት። 14ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ስለራሴ ብመሰክርም ምስክርነቴ እውነት ነው፤ ከየት እንደመጣሁ፥ ወዴት እንደምሄድም አውቃለሁና፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወዴት እንደምሄድም አታውቁም። 15እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ ግን በማንም አልፈርድም። 16እኔ ብፈርድም እውነትን እፈርዳለሁ፤ እኔና የላከኝ አብ ነን እንጂ አንድ ብቻዬን አይደለሁምና። 17የሁለት ሰዎች ምስክርነት የታመነ እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል። 18እኔ ስለ ራሴ ምስክር ነኝ፤ የላከኝ አብም ይመሰክርልኛል።” 19እነርሱም፥ “አባትህ የት ነው?” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔን አታውቁም፤ አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” ብሎ መለሰላቸው። 20ጌታችን ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ሲያስተምራቸው በሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ይህን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልያዙትም፤ ጊዜው ገና አልደረሰም ነበርና።
አይሁድ ጌታችን ወደሚሄድበት መሄድ ስላለመቻላቸው
21ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “እኔ እሄዳለሁ ትሹኛላችሁም፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤#“አታገኙኝም” የሚለው በግሪኩ የለም። በኀጢኣታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበትም እናንተ መምጣት አይቻላችሁም” አላቸው። 22አይሁድም፥ “እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አትችሉም የሚለን እርሱ ራሱን ይገድል ይሆን? እንጃ!” አሉ። 23እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “እናንተስ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይደለሁም። 24እነሆ፥ በኀጢኣታችሁ ትሞታላችሁ እንዳልኋችሁ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ባታምኑ በኀጢኣትችሁ ትሞታላችሁ።” 25እነርሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “በመጀመሪያ ነግሬአችኋለሁ። 26ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ አለኝ፤ የላከኝም እውነተኛ ነው፤ እኔ በእርሱ ዘንድ የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።” 27ነገር ግን ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም። 28ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ በአደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ፤ አባቴ እንደ አስተማረኝም እንዲሁ እናገራለሁ እንጂ የምናገረው ከእኔ አይደለም። 29የላከኝም ከእኔ ጋር አለ፤ አብ ብቻዬን አይተወኝም፤ እኔም ዘወትር ደስ የሚያሰኘውን አደርጋለሁ።” 30ይህንም በተናገረ ጊዜ ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
ከአይሁድ ወገን ላመኑት የተነገረ
31ጌታችን ኢየሱስም ያመኑበትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተም በቃሌ ጸንታችሁ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ። 32እውነትንም ታውቋታላችሁ፤ እውነትም አርነት ታወጣችኋለች።” 33#ማቴ. 3፥9፤ ሉቃ. 3፥8። እነርሱም መልሰው፥ “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማንም ከቶ ባሮች አልሆንም፤ እንግዲህ እንዴት አርነት ትወጣላችሁ ትለናለህ?” አሉት።
34ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢኣትን የሚሠራ ሁሉ የኀጢኣት ባርያ ነው። 35ባርያ ዘወትር በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለዓለም ይኖራል። 36ወልድ አርነት ካወጣችሁ በእውነት አርነት የወጣችሁ ናችሁ። 37የአብርሃም ዘር እንደ ሆናችሁስ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ ዘንድ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትሻላችሁ። 38እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም በአባታችሁ ያያችሁትን#በግሪኩ “የሰማችሁትን” ይላል። ታደርጋላችሁ።” 39እነርሱም መልሰው፥ “የእኛስ አባታችን አብርሃም ነው” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር። 40አሁንም በእግዚአብሔር ዘንድ የሰማሁትን እውነት የምነግራችሁን#አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “ጻድቅ” የሚል ይጨምራል። ሰው ልትገድሉኝ ትሻላችሁ፤ አብርሃምስ እንዲህ አላደረገም። 41እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፥ “እኛ ከዝሙት አልተወለድንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት። 42ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንስ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመጣሁ አይደለሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ። 43እንግዲህ ቃሌን ለምን አታስተውሉም? ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። 44እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና። 45እኔ ግን እውነትን እናገራለሁና አታምኑኝም። 46ስለ ኀጢኣት ከእናንተ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እኔ እውነት የምናገር ከሆንሁ ለምን አታምኑኝም? 47ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ ስለዚህ እናንተ አትሰሙኝም፤ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና።”
48አይሁድም፥ “አንተ ሳምራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔንም እንደ አለብህ መናገራችን በሚገባ አይደለምን?” ብለው ጠየቁት። 49ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ትንቁኛላችሁ። 50እኔ ለራሴ ክብርን አልሻም፤ የሚሻ፥ የሚፈርድም አለ። 51እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም።” 52አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ። 53በውኑ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም፥ አንተ ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞቱ፤ ራስህን ማን ታደርጋለህ?” 54ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ምንም አይጠቅመኝም፤ የሚያከብረኝስ እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ አለ። 55እናንተም አታውቁትም፤ እኔ ግን ኣውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብልም እንደ እናንተ ሐሰተኛ እሆናለሁ፤ እኔ አውቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ። 56አባታችሁ አብርሃም የእኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤#ግሪኩ “ሐሤት አደረገ” ይላል። አይቶም ደስ አለው።” 57አይሁድም፥ “ገና አምሳ ዓመት ያልሞላህ እንዴት አብርሃምን አየህ?” አሉት። 58ጌታችን ኢየሱስም፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ።” አላቸው። 59ሊደበድቡትም ድንጋይ አነሡ፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው፤ ከቤተ መቅደስም ወጣ፤ በመካከላቸውም አልፎ ሄደ።
S'ha seleccionat:
የዮሐንስ ወንጌል 8: አማ2000
Subratllat
Comparteix
Copia
Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió

: