ኦሪት ዘፍጥረት 8
8
1እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ። 2እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፉስን አሳለፈ፤ ውኂውም ጎደለ የቀላዪም ምንጮች የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፤ 3ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ ውኂውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኂው ጎደለ። 4መርከቢቱም በስባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች፤ ላይ ተቀመጠች። 5ውኂውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበረ፤ በአሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበር በአሥረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮች ራሶች ተገለጡ።
6ከአርባ ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፤ 7ቁራንም ሰደደው እርሱም ወጣ፤ ውኂው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። 8ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት። 9ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አለገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ እጁን ዘረጋና ተቀበላት ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት። 10ከዚያም በኋላ ደግሞ እስከ ስባት ቀን ቆየ ርግንም እንደ ገና ከመርከብ ሰደደ። 11ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ። 12ደግሞ እስከ ሰባት ቀም ቆየ ርግብንም ሰደዳት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልስተመለሰችም።
13በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ክዳን አነሣ፥ እነሆም ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። 14በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛውም ወር ቀን ምድር ደረቀች።
15እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ 16አንተ ሚስትህንና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ። 17ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይብዙ። 18ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ። 19አራዊት ሁሉ፥ ተቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ በምድር ላይ የሚርመሰምስው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ።
20ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ። 21እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ ምድርን ዳግመኛ ስለ ስው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉት እንደ ገና አልመታም። 22በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።
S'ha seleccionat:
ኦሪት ዘፍጥረት 8: አማ54
Subratllat
Comparteix
Copia
Vols que els teus subratllats es desin a tots els teus dispositius? Registra't o inicia sessió