1
የሉቃስ ወንጌል 21:36
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።”
Σύγκριση
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:36
2
የሉቃስ ወንጌል 21:34
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:34
3
የሉቃስ ወንጌል 21:19
በትዕግሥታችሁ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ” አለ።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:19
4
የሉቃስ ወንጌል 21:15
ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:15
5
የሉቃስ ወንጌል 21:33
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:33
6
የሉቃስ ወንጌል 21:25-27
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ ከዚህም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ላይ ሆኖ ሲመጣ ሰዎች ያዩታል።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:25-27
7
የሉቃስ ወንጌል 21:17
ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:17
8
የሉቃስ ወንጌል 21:11
በየቦታውም ብርቱ የምድር መናወጥ፥ ራብና ወረርሽኝ ይሆናል። የሚያስፈሩ ነገሮችና ታላላቅ ምልክቶች በሰማይ ላይ ይታያሉ።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:11
9
የሉቃስ ወንጌል 21:9-10
ስለ ጦርነትና ስለ ሁከት በምትሰሙበት ጊዜም አትደንግጡ፤ አስቀድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ይሁን እንጂ ፍጻሜው ወዲያውኑ አይሆንም።” ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:9-10
10
የሉቃስ ወንጌል 21:25-26
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:25-26
11
የሉቃስ ወንጌል 21:10
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:10
12
የሉቃስ ወንጌል 21:8
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
Διαβάστε የሉቃስ ወንጌል 21:8
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο