ኦሪት ዘፍጥረት 12
12
የአብራም መጠራት
1 #
ጥበ. 10፥5፤ የሐዋ. 7፥2፤3፤ ዕብ. 11፥8። እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። 2ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ ለበረከትም ትሆናለህ፤
3 #
ገላ. 3፥8። የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥
የሚረግሙህንም እረግማለሁ፥
የምድር ነገዶችም ሁሉ
በአንተ ይባረካሉ።
4አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። 5አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ። 6አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የባሉጥ ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፥ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። 7#የሐዋ. 7፥5፤ ገላ. 3፥16።እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። 8ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ። 9አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።
አብራም በግብጽ አገር
10በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና። 11ወደ ግብጽም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራን እንዲህ አላት፦ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፥ 12የግብጽ ሰዎች ያዩሽ እንደሆነ፦ ሚስቱ ናት ይላሉ፥ እኔንም ይገድሉኛል፥ አንቺንም በሕይወት ይተዉሻል። 13#ዘፍ. 20፥2፤ 26፥7።እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ፥ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ፦ እኅቱ ነኝ በዪ።#12፥13 ይህ ሁኔታ ከላይኛው ሜሶጰጣሚያ የጠለፋ ባህል ውስጥ የተወሰደ ነው፥ ተብሎ ተገልጧል። የሕግ ሚስትን እንደ እኅት መርጦ የሚያዝበት፥ በኋላም ከፍተኛ ጥበቃና የበለጠ ማህበራዊ ዕውቅና የሚደረግበት ባሕል በጥንታዊያን ማኅበረሰቦች ዘንድ እንደ ነበር ይገመታል። በሣራ ላይም ይህ ዓይነቱ ነገር ተከስቷል። ሆኖም አብርሃም ከአደጋ ለማምለጥ ሲል የሳራን ሚስትነት ሳይገልጽ እኅትነቷን ለመመስከር ወደደ። 14አብራምም ወደ ግብጽ በገባ ጊዜ የግብጽ ሰዎች ሴቲቱ እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፥ 15የፈርዖንም አለቆች አዩአት፥ በፈርዖንም ፊት አመሰገኑአት፥ ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት። 16ለአብራምም በእርሷ ምክንያት መልካም አደረገለት፥ ለእርሱ በጎችም በሬዎችም አህዮችም ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችም ግመሎችም ነበሩት። 17እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ። 18ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብኝ ምንድነው? እርሷ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም? 19ለምንስ፦ እኅቴ ናት አልህ? እኔ ሚስት ላደርጋት ወስጄአት ነበር። አሁንም ሚስትህ እነኋት፥ ይዘሃት ሂድ። 20ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው።
Επιλέχθηκαν προς το παρόν:
ኦሪት ዘፍጥረት 12: መቅካእኤ
Επισημάνσεις
Κοινοποίηση
Αντιγραφή
Θέλετε να αποθηκεύονται οι επισημάνσεις σας σε όλες τις συσκευές σας; Εγγραφείτε ή συνδεθείτε

: