የሉ​ቃስ ወን​ጌል 17

17
ስለ ጥፋት መም​ጣት
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መሰ​ና​ክል ግድ ይመ​ጣል፤ ነገር ግን መሰ​ና​ክ​ልን ለሚ​ያ​መ​ጣት ሰው ወዮ​ለት። 2ከእ​ነ​ዚህ ከታ​ና​ና​ሾቹ አን​ዱን ከሚ​ያ​ሰ​ና​ክል ይልቅ አህያ የሚ​ፈ​ጭ​በት የወ​ፍጮ ድን​ጋይ በአ​ን​ገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰ​ጥም በተ​ሻ​ለው ነበር። 3#ማቴ. 18፥15። ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ወን​ድ​ምህ አን​ተን ቢበ​ድል ብቻ​ህን ምከ​ረው፤ ቢጸ​ጸት ግን ይቅር በለው። 4በየ​ቀኑ ሰባት ጊዜ ቢበ​ድ​ልም ሰባት ጊዜ ከተ​ጸ​ጸተ ይቅር በለው።”
ስለ ሃይ​ማ​ኖት ኀይል
5ሐዋ​ር​ያ​ትም ጌታን፥ “እም​ነ​ትን ጨም​ር​ልን” አሉት። 6ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣት ታህል እም​ነት ብት​ኖ​ራ​ችሁ ይህ​ችን ሾላ ከሥ​ርሽ ተነ​ቅ​ለሽ በባ​ሕር ውስጥ ተተ​ከዪ ብት​ሉ​አት ትታ​ዘ​ዝ​ላ​ች​ኋ​ለች።”
ስለ መታ​ዘዝ
7“አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን? 8እራ​ቴን አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፥ እስ​ክ​በ​ላና እስ​ክ​ጠጣ ድረ​ስም ታጥ​ቀህ አሳ​ል​ፍ​ልኝ፤ ከዚ​ህም በኋላ አንተ ብላ፥ ጠጣም ይለው የለ​ምን? 9እን​ግ​ዲህ ጌታው ያዘ​ዘ​ውን ሥራ​ውን ቢሠራ ለዚያ አገ​ል​ጋይ ምስ​ጋና አለ​ውን? 10እን​ዲሁ እና​ን​ተም ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ር​ጋ​ችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ነን፤ ለመ​ሥ​ራ​ትም የሚ​ገ​ባ​ንን ሠራን’ በሉ።”
ዐሥ​ሩን ለም​ጻ​ሞች እን​ዳ​ነጻ
11ከዚህ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሲሄድ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ መካ​ከል ዐለፈ። 12ወደ አን​ዲት መን​ደ​ርም ሲገባ ለምጽ የያ​ዛ​ቸው ዐሥር ሰዎች ተቀ​በ​ሉ​ትና ራቅ ብለው ቆሙ። 13ድም​ጻ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው፥ “ጌታ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ እዘ​ን​ልን” አሉ። 14#ዘሌ. 14፥1-32። ባያ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ ካህን ሂዱና ራሳ​ች​ሁን አስ​መ​ር​ምሩ” አላ​ቸው፤ ሲሄ​ዱም ነጹ። 15ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ እንደ ነጻ ባየ ጊዜ፥ በታ​ላቅ ቃል እያ​መ​ሰ​ገነ ተመ​ለሰ። 16በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር። 17ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፤ “የነጹ ዐሥር አል​ነ​በ​ሩ​ምን? እን​ግ​ዲህ ዘጠኙ የት አሉ? 18ወገኑ ሌላ ከሆነ ከዚህ ሰው በቀር ለእ​ነ​ዚያ ተመ​ልሶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገን ተሳ​ና​ቸ​ውን?” 19እር​ሱ​ንም፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ እም​ነ​ትህ አዳ​ነ​ችህ” አለው።
ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መም​ጣት
20ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም። 21እን​ኋት፥ በዚህ ናት፤ ወይም እነ​ኋት፥ በዚያ ናት አይ​ሉ​አ​ትም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትስ እነ​ኋት፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ናት።”
22ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከሰው ልጆች ቀኖች አን​ዲ​ቱን ታዩ ዘንድ የም​ት​መ​ኙ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ነገር ግን አታ​ዩ​አ​ትም። 23እነሆ፥ በዚህ ነው፥ ወይም እነሆ፥ በዚያ ነው ቢሉ​አ​ችሁ አት​ውጡ፤ አት​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም። 24መብ​ረቅ ብልጭ ብሎ ከሰ​ማይ ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ እን​ደ​ሚ​ያ​በራ የሰው ልጅ አመ​ጣጡ እን​ዲሁ ነውና። 25ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ብዙ መከ​ራን ይቀ​በ​ላል፤ ይህች ትው​ል​ድም ትን​ቀ​ዋ​ለች፤ ትፈ​ታ​ተ​ነ​ዋ​ለ​ችም። 26#ዘፍ. 6፥5-8። በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲሁ ይሆ​ናል። 27#ዘፍ. 7፥6-24። ኖኅ ወደ መር​ከብ እስከ ገባ​በት ቀን ድረስ ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ሲያ​ገ​ቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥ​ፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድ​ርጎ አጠፋ። 28በሎጥ ዘመ​ንም ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ቤት ሲሠ​ሩና ተክል ሲተ​ክሉ፥ ሲሸ​ጡና ሲገዙ ነበረ። 29#ዘፍ. 18፥20—19፥25። ሎጥ ከሰ​ዶም በወ​ጣ​በት ቀን ግን ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን ዘነመ፤ ሁሉ​ንም አጠፋ። 30የሰው ልጅም በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እን​ዲሁ ይሆ​ናል፤ አይ​ታ​ወ​ቅ​ምም። 31#ማቴ. 24፥17-18፤ ማር. 13፥15-16። ያን​ጊ​ዜም በሰ​ገ​ነት ላይ ያለ፥ ገን​ዘ​ቡም በም​ድር ቤት የሆ​ነ​በት ሰው ለመ​ው​ሰድ አይ​ው​ረድ፤ በዱር ያለም ወደ ኋላው አይ​መ​ለስ። 32#ዘፍ. 19፥26። የሎ​ጥን ሚስት ዐስ​ቡ​አት። 33#ማቴ. 10፥39፤ 16፥25፤ ማር. 8፥35፤ ሉቃ. 9፥24፤ ዮሐ. 12፥25። ነፍ​ሱን ሊያ​ድ​ናት የሚ​ወድ ይጣ​ላት፤ ስለ እኔ#“ስለ እኔ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ያድ​ና​ታል። 34እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሁለት ሰዎች በአ​ንድ አልጋ ይተ​ኛሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ። 35ሁለት ሴቶ​ችም በአ​ንድ ወፍጮ ይፈ​ጫሉ፤ አን​ዲ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ይተ​ዋሉ። 36ሁለት ሰዎች በአ​ንድ እርሻ ላይ ይኖ​ራሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ።” 37እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አቤቱ፥ ወዴት ነው?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ገደላ በአ​ለ​በት አሞ​ሮች በዚያ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ” አላ​ቸው።

اکنون انتخاب شده:

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 17: አማ2000

های‌لایت

به اشتراک گذاشتن

کپی

None

می خواهید نکات برجسته خود را در همه دستگاه های خود ذخیره کنید؟ برای ورودثبت نام کنید یا اگر ثبت نام کرده اید وارد شوید