የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 8

8
ስለ አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ሴት ፍርድ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። 2በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር። 3ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በዝ​ሙት የተ​ያ​ዘች ሴት ወደ እርሱ አም​ጥ​ተው በመ​ካ​ከል አቆ​ሙ​አት። 4እን​ዲ​ህም አሉት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይቺን ሴት ስታ​መ​ነ​ዝር አግ​ኝ​ተን ያዝ​ናት። 5#ዘሌ. 20፥10፤ ዘዳ. 22፥22-24። እን​ደ​ዚ​ችም ያለ​ችው በድ​ን​ጋይ እን​ድ​ት​ደ​በ​ደብ ሙሴ በኦ​ሪት አዘ​ዘን፤ እን​ግ​ዲህ አንተ ስለ እር​ስዋ ምን ትላ​ለህ?” 6በእ​ር​ሱም ላይ ምክ​ን​ያት ሊያ​ገኙ ሲፈ​ት​ኑት ይህን አሉ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ። 7ብዙ ጊዜ መላ​ል​ሰው በጠ​የ​ቁት ጊዜም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ፥ “ከእ​ና​ንተ ኀጢ​ኣት የሌ​ለ​በት አስ​ቀ​ድሞ ድን​ጋይ ይጣ​ል​ባት” አላ​ቸው። 8ዳግ​መ​ኛም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ። 9እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር። 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀና ብሎ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚ​ከ​ሱሽ ወዴት አሉ?” 11እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማ​የው የለም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም አል​ፈ​ር​ድ​ብ​ሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ ኀጢ​ኣት አት​ሥሪ” አላት።
ኢየ​ሱስ የዓ​ለም ብር​ሃን
12 # ማቴ. 5፥14፤ ዮሐ. 9፥5። ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። 13#ዮሐ. 5፥31። ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “አንተ ስለ ራስህ ትመ​ሰ​ክ​ራ​ለህ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ምስ​ክ​ር​ነ​ትህ እው​ነት አይ​ደ​ለም” አሉት። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ስለ​ራሴ ብመ​ሰ​ክ​ርም ምስ​ክ​ር​ነቴ እው​ነት ነው፤ ከየት እን​ደ​መ​ጣሁ፥ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እና​ንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አታ​ው​ቁም። 15እና​ንተ ሥጋዊ ፍር​ድን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኔ ግን በማ​ንም አል​ፈ​ር​ድም። 16እኔ ብፈ​ር​ድም እው​ነ​ትን እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔና የላ​ከኝ አብ ነን እንጂ አንድ ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና። 17የሁ​ለት ሰዎች ምስ​ክ​ር​ነት የታ​መነ እንደ ሆነ በሕ​ጋ​ችሁ ተጽ​ፎ​አል። 18እኔ ስለ ራሴ ምስ​ክር ነኝ፤ የላ​ከኝ አብም ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል።” 19እነ​ር​ሱም፥ “አባ​ትህ የት ነው?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔን አታ​ው​ቁም፤ አባ​ቴ​ንም አታ​ው​ቁም፤ እኔ​ንስ ብታ​ውቁ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው። 20ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።
አይ​ሁድ ጌታ​ችን ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በት መሄድ ስላ​ለ​መ​ቻ​ላ​ቸው
21ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “እኔ እሄ​ዳ​ለሁ ትሹ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኙ​ኝም፤#“አታ​ገ​ኙ​ኝም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ች​ሁም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው። 22አይ​ሁ​ድም፥ “እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም የሚ​ለን እርሱ ራሱን ይገ​ድል ይሆን? እንጃ!” አሉ። 23እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተስ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ፤ እና​ንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ሁም። 24እነሆ፥ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ባታ​ምኑ በኀ​ጢ​ኣ​ት​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።” 25እነ​ር​ሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በመ​ጀ​መ​ሪያ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ። 26ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።” 27ነገር ግን ስለ አብ እንደ ነገ​ራ​ቸው አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም። 28ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ውን ልጅ ከፍ ከፍ በአ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ አባቴ እንደ አስ​ተ​ማ​ረ​ኝም እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ የም​ና​ገ​ረው ከእኔ አይ​ደ​ለም። 29የላ​ከ​ኝም ከእኔ ጋር አለ፤ አብ ብቻ​ዬን አይ​ተ​ወ​ኝም፤ እኔም ዘወ​ትር ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን አደ​ር​ጋ​ለሁ።” 30ይህ​ንም በተ​ና​ገረ ጊዜ ብዙ​ዎች በእ​ርሱ አመኑ።
ከአ​ይ​ሁድ ወገን ላመ​ኑት የተ​ነ​ገረ
31ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያመ​ኑ​በ​ትን አይ​ሁድ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ን​ተም በቃሌ ጸን​ታ​ችሁ ብት​ኖሩ በእ​ው​ነት ደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ናችሁ። 32እው​ነ​ት​ንም ታው​ቋ​ታ​ላ​ችሁ፤ እው​ነ​ትም አር​ነት ታወ​ጣ​ች​ኋ​ለች።” 33#ማቴ. 3፥9፤ ሉቃ. 3፥8። እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “እኛ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማ​ንም ከቶ ባሮች አል​ሆ​ንም፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አር​ነት ትወ​ጣ​ላ​ችሁ ትለ​ና​ለህ?” አሉት።
34ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ሠራ ሁሉ የኀ​ጢ​ኣት ባርያ ነው። 35ባርያ ዘወ​ትር በቤት አይ​ኖ​ርም፤ ልጅ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል። 36ወልድ አር​ነት ካወ​ጣ​ችሁ በእ​ው​ነት አር​ነት የወ​ጣ​ችሁ ናችሁ። 37የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንደ ሆና​ች​ሁስ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ኖ​ር​ምና ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ። 38እኔ በአ​ባቴ ዘንድ ያየ​ሁ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በአ​ባ​ታ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ትን#በግ​ሪኩ “የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን” ይላል። ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።” 39እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “የእ​ኛስ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ነው” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ብት​ሆ​ኑስ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሥራ በሠ​ራ​ችሁ ነበር። 40አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ጻድቅ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም። 41እና​ንተ ግን የአ​ባ​ታ​ች​ሁን ሥራ ትሠ​ራ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከዝ​ሙት አል​ተ​ወ​ለ​ድ​ንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው” አሉት። 42ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ታ​ችሁ ቢሆ​ንስ እኔን በወ​ደ​ዳ​ች​ሁኝ ነበር፤ እኔ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቼ መጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ። 43እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው። 44እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና። 45እኔ ግን እው​ነ​ትን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና አታ​ም​ኑ​ኝም። 46ስለ ኀጢ​ኣት ከእ​ና​ንተ የሚ​ወ​ቅ​ሰኝ ማን ነው? እኔ እው​ነት የም​ና​ገር ከሆ​ንሁ ለምን አታ​ም​ኑ​ኝም? 47ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ እና​ንተ አት​ሰ​ሙ​ኝም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና።”
48አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት። 49ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አባ​ቴን አከ​ብ​ራ​ለሁ እንጂ ጋኔን የለ​ብ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ትን​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ። 50እኔ ለራሴ ክብ​ርን አል​ሻም፤ የሚሻ፥ የሚ​ፈ​ር​ድም አለ። 51እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም።” 52አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ። 53በውኑ ከሞ​ተው ከአ​ባ​ታ​ችን ከአ​ብ​ር​ሃም፥ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? ነቢ​ያ​ትም ሞቱ፤ ራስ​ህን ማን ታደ​ር​ጋ​ለህ?” 54ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ራሴን ባከ​ብር ክብሬ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም፤ የሚ​ያ​ከ​ብ​ረ​ኝስ እና​ንተ አም​ላ​ካ​ችን የም​ት​ሉት አባቴ አለ። 55እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ እኔ ግን ኣው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ አላ​ው​ቀ​ውም ብልም እንደ እና​ንተ ሐሰ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔ አው​ቀ​ዋ​ለሁ ቃሉ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ። 56አባ​ታ​ችሁ አብ​ር​ሃም የእ​ኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤#ግሪኩ “ሐሤት አደ​ረገ” ይላል። አይ​ቶም ደስ አለው።” 57አይ​ሁ​ድም፥ “ገና አምሳ ዓመት ያል​ሞ​ላህ እን​ዴት አብ​ር​ሃ​ምን አየህ?” አሉት። 58ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አብ​ር​ሃም ሳይ​ወ​ለድ እኔ አለሁ።” አላ​ቸው። 59ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።

Kiemelés

Megosztás

Másolás

None

Szeretnéd, hogy a kiemeléseid minden eszközödön megjelenjenek? Regisztrálj vagy jelentkezz be