ኦሪት ዘፍጥረት 7
7
1እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና። 2ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ 3ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። 4ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና። 5ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። 6ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። 7ኖኅም ስለ ጥፋት ውኂ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ። 8ከንጽሕ እንስሳ ንጽሕም ካልሆነው እንስሳ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀስውም ሁሉ፤ 9እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። 10ከሰባት ቀንም በኍላ የጥፋት ውኂ በምድር ላይ ሆነ። 11በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ 12የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ ዝናቡም አርባ ቀንም አርባ ሌሊት በምድት ላይ ሆነ።
13በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ። 14እነርሱ አራዊትም ሂሉ በየወገናቸው፤ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው በንድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው 15የሚበሩ ወፎችም ሁሉ ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። 16ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት። 17የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። 18ውኂውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱም በውኂ ላይ ሄደች። 19ውኂውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሽነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ። 20ውኂው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ። 21በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቃሹም ሁሉ ሰውም ሁሉ ጠፉ። 22በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። 23በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። 24ውኅውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።
Jelenleg kiválasztva:
ኦሪት ዘፍጥረት 7: አማ54
Kiemelés
Megosztás
Másolás
Szeretnéd, hogy a kiemeléseid minden eszközödön megjelenjenek? Regisztrálj vagy jelentkezz be

: