1
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔር አምላክም ለኖኅ አለው፥ “በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም ትውልድ የማደርገው የቃል ኪዳኔ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስቴን በደመና አኖራለሁ፤ የቃል ኪዳኔም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
비교
ኦሪት ዘፍጥረት 9:12-13 살펴보기
2
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16
ቀስቴም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር መካከል፥ በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘለዓለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 9:16 살펴보기
3
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6
የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ስለዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሬዋለሁና።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:6 살펴보기
4
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:1 살펴보기
5
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3
ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ፤ ሁሉንም እንደ ለመለመ ቡቃያ ሰጠኋችሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:3 살펴보기
6
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይ ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነርሱንም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
ኦሪት ዘፍጥረት 9:2 살펴보기
7
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7
እናንተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም።”
ኦሪት ዘፍጥረት 9:7 살펴보기
홈
성경
묵상
동영상