1
ዘፍጥረት 9:12-13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Palyginti
Naršyti ዘፍጥረት 9:12-13
2
ዘፍጥረት 9:16
ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”
Naršyti ዘፍጥረት 9:16
3
ዘፍጥረት 9:6
“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) አምሳል፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰውን ሠርቶታልና።
Naršyti ዘፍጥረት 9:6
4
ዘፍጥረት 9:1
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤
Naršyti ዘፍጥረት 9:1
5
ዘፍጥረት 9:3
ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
Naršyti ዘፍጥረት 9:3
6
ዘፍጥረት 9:2
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በዱር አራዊት፣ በሰማይ አዕዋፍ፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች ሁሉ ላይ ይሁን፤ በእጃችሁ ተሰጥተዋል።
Naršyti ዘፍጥረት 9:2
7
ዘፍጥረት 9:7
እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ፤ ይንሰራፋ።”
Naršyti ዘፍጥረት 9:7
Pradžia
Biblija
Planai
Vaizdo įrašai