1
ማርቆስ 13:13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በእኔ ምክንያት በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል።
နှိုင်းယှဉ်
ማርቆስ 13:13ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
ማርቆስ 13:33
ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፣ ጸልዩም።
ማርቆስ 13:33ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
ማርቆስ 13:11
ተይዛችሁ ለፍርድ በምትቀርቡበት ጊዜ፣ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
ማርቆስ 13:11ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
ማርቆስ 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።
ማርቆስ 13:31ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
ማርቆስ 13:32
“ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያችም ሰዓት ከአብ በቀር፣ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ ወልድም ቢሆን፣ ማንም አያውቅም።
ማርቆስ 13:32ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
ማርቆስ 13:7
ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።
ማርቆስ 13:7ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
ማርቆስ 13:35-37
እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፣ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ፤ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ተግታችሁ ጠብቁ!”
ማርቆስ 13:35-37ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
8
ማርቆስ 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
ማርቆስ 13:8ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
9
ማርቆስ 13:10
አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።
ማርቆስ 13:10ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
10
ማርቆስ 13:6
ብዙዎች፣ ‘እኔ እርሱ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
ማርቆስ 13:6ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
11
ማርቆስ 13:9
“ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለአካባቢ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዦችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
ማርቆስ 13:9ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
12
ማርቆስ 13:22
ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፣ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ።
ማርቆስ 13:22ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
13
ማርቆስ 13:24-25
“በዚያን ጊዜ፣ ከመከራው በኋላ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፣ “ ‘ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።’
ማርቆስ 13:24-25ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ