YouVersion लोगो
खोज आइकन

የሉቃስ ወንጌል 14

14
ኢየሱስ አንድ በሽተኛ በሰንበት ቀን እንደ ፈወሰ
1በሰንበትም ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር። 2እነሆም፥ ሰውነቱ በሙሉ ያበጠበት ሰው በፊቱ ነበረ። 3ኢየሱስም መልሶ “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” ብሎ ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን ጠየቀ። 4እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው። 5#ማቴ. 12፥11።“ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጉድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው። 6ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
ስለ ትሕትናና ስለ መስተንግዶ
7የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል 8#ምሳ. 25፥6-7።“ማንም ለሰርግ ቢጠራህ በከበሬታ ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ተጠርቶ ይሆናልና፥ አንተንና እርሱን የጠራ መጥቶ 9‘ለዚህ ሰው ስፍራ ተውለት’ ይልሃል፤ በዚያን ጊዜም እያፈርህ ዝቅተኛውን ስፍራ መያዝ ትጀምራለህ። 10ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ ‘ወዳጄ ሆይ! ወደ ላይ ውጣ’ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል። 11#ማቴ. 23፥12፤ ሉቃ. 18፥14።ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
12የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው “ምሳ ወይም እራት ባሰናዳህ ጊዜ፥ ምናልባት እነርሱም በተራቸው እንዳይጠሩህ፥ እንዳይክሱህም፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ሀብታም ጎረቤቶችህንም አትጥራ። 13ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤ 14የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”
የታላቁ ግብዣ ምሳሌ
(ማቴ. 22፥1-10)
15በማእድ ከተቀመጡትም አንዱ ይህን ሰምቶ “በእግዚአብሔር መንግሥት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው፤” አለው። 16እርሱ ግን እንዲህ አለው “አንድ ሰው ታላቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን ጠራ፤ 17በእራትም ሰዓት የታደሙትን ‘አሁን ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ኑ’ እንዲላቸው አገልጋዩን ላከ። 18ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የመጀመሪያው ‘መሬት ገዝቼአለሁ፤ ወጥቼም ላየው የግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤’ አለው። 19ሌላውም ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቼአለሁ፤ ለመፈተንም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤’ አለው። 20ሌላውም ‘ሚስት አግብቼአለሁ፤ ስለዚህም ልመጣ አልችልም’ አለው። 21አገልጋዩም መልሶ ይህንን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ አገልጋዩን ‘ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች መንገዶች ውጣ፤ ድሆችንና ጉንድሾችን ና ዐይነ ስውሮችንና አንካሶችንም ወደዚህ አስገባ፤’ አለው። 22አገልጋዩም ‘ጌታ ሆይ! እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፤ ሆኖም ገና ስፍራ አለ፤’ አለው። 23ጌታውም አገልጋዩን ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣና እንዲገቡ ገፋፋቸው፤ 24ተጋብዘው ከነበሩት ከእነዚያ ሰዎች አንድ እንኳን እራቴን አይቀምስም እላችኋለሁ፤’ አለው።”
ኢየሱስን መከተል መሥዋዕትነትን እንደሚጠይቅ
(ማቴ. 10፥37-38)
25ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤ ዘወር ብሎም እንዲህ አላቸው 26#ማቴ. 10፥37።“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 27#ማቴ. 10፥38፤ 16፥24፤ ማር. 8፥34፤ ሉቃ. 9፥23።ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 28ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ እንዳለው አስቀድሞ ተቀምጦ ወጪውን የማይቈጥር ማን ነው? 29ያለዚያ መሠረቱን ቢያኖር፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ 30‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ። 31ወይንም በጦርነት ሌላውን ሊጋጠም የሚሄድ ንጉሥ፥ ሃያ ሺህ ሰው አስከትቶ የሚመጣበትን በዐሥር ሺህ ሰው ሊገጥም ይችል እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ማን ነው? 32ካልሆነም ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልእክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል። 33እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ማንም ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
የማይጠቅም ጨው
(ማቴ. 5፥13ማር. 9፥50)
34“ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? 35ለምድርም ሆነ ለፍግ መቈለያ አይጠቅምም፤ ወደ ውጭም ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”

अहिले सेलेक्ट गरिएको:

የሉቃስ ወንጌል 14: መቅካእኤ

हाइलाइट

शेयर गर्नुहोस्

कपी गर्नुहोस्

None

तपाईंका हाइलाइटहरू तपाईंका सबै यन्त्रहरूमा सुरक्षित गर्न चाहनुहुन्छ? साइन अप वा साइन इन गर्नुहोस्