የሉቃስ ወንጌል 5
5
የስምዖን ጴጥሮስና የዘብዴዎስ ልጆች መጠራት
(ማቴ. 4፥18-22፤ ማር. 1፥16-20)
1 #
ማቴ. 13፥1፤2፤ ማር. 3፥9፤10፤ 4፥1። እርሱም በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ፥ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በዙርያው ይጋፉ ነበር፤ 2በባሕሩ ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። 3ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደነበረችው ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር። 4ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው። 5#ዮሐ. 21፥3።ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው። 6#ዮሐ. 21፥6።ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። 7በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። 8ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው። 9እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስላጠመዱት ዓሣ ተደንቀው ነበርና፤ 10እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ወዳጆች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው። 11ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።
ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው ማንጻቱ
(ማቴ. 8፥1-4፤ ማር. 1፥40-45)
12ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ፦ “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ተማጸነው። 13እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው። 14#ዘሌ. 14፥1-32።እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ ነገር ግን፦ “ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ፤” አለው። 15ስለ እርሱ የሚባለው ግን ይበልጡን በስፋት ተሰራጨ፤ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ 16እርሱ ግን ገለል ብሎ ወደ በምድረ በዳዎች እየሄደ ይጸልይ ነበር።
ኢየሱስ ሽባውን ሰው መፈወሱ
(ማቴ. 9፥1-8፤ ማር. 2፥1-12)
17እንዲህም ሆነ፤ አንድ ቀን ሲያስተምር ሳለ ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ ከኢየሩሳሌምም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ የሚፈውስበትም የጌታ ኃይል ከእርሱ ጋር ነበረ። 18እነሆም፥ አንድ መንቀሳቀስ የማይችል ሰው በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አስገብተውትም በፊቱ ሊያኖሩት ይፈልጉ ነበር። 19ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ እርሱን ለማስገባት ምንም ዓይነት መንገድ ባለማግኘታቸው ወደ ሰገነቱ ወጡ፤ የጣራውንም ጡብ አሳልፈው በመካከላቸው ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አወረዱት። 20እምነታቸውንም አይቶ እንዲህ አለ፦ “አንተ ሰው! ኀጢአቶችህ ተሰረዩልህ።” 21ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ “ስድብን የሚሰነዝር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ማን ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ይችላል?” እያሉ ያስቡ ነበር። 22ኢየሱስም ሐሳባቸውን ባወቀ ጊዜ መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “በልባችሁ ምን እያሰባችሁ ነው? 23‘ኀጢአቶችህ ተሰረዩልህ፤’ ከማለትና ‘ተነሣና ሂድ፤’ ከማለት የትኛው ይቀላል? 24ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” ብሎ፥ መንቀሳቅስ የተሳነውን ሰው፦ “እነሆ አዝሃለሁ፤ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው። 25ወዲያውኑ በፊታቸው ተነሣ፤ ተኝቶበትም የነበረውን ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። 26ሁሉም ተገረሙ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ በፍርሃትም ተሞልተው፦ “ዛሬስ አስደናቂ ነገሮችን አየን፤” አሉ።
ማቴዎስ የተባለው ሌዊ እንደ ተጠራ
(ማቴ. 9፥9-13፤ ማር. 2፥13-17)
27ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሌዊ የሚባል ቀራጭ በመቅረጫው ስፍራ ተቀምጦ ተመለከተና፦ “ተከተለኝ፤” አለው። 28እርሱም ሁሉንም ነገር ትቶ፤ ተነሥቶ ተከተለው።
29ሌዊም ታላቅ ግብዣ በቤቱ አደረገለት፤ ከቀራጮችና ከሌሎችም ብዙ ሕዝብ በማዕድ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው ነበር። 30#ሉቃ. 15፥1፤2።ፈሪሳውያንና ጻፎቻቸውም፦ “ስለምን ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ትበላላችሁ? ትጠጣላችሁም?” ብለው በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጉረመረሙ። 31ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤ 32ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
ስለ ጾም የቀረበ ጥያቄ
(ማቴ. 9፥4-18፤ ማር. 2፥18-24)
33እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።” 34ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታጾሙ አትችሉም፤ ትችላላችሁን? 35ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀኖች ይመጣሉ፤ በነዚያ ቀኖች ይጾማሉ።” 36እንዲህ ሲልም በምሳሌ ነገራቸው፦ “የአዲስ ልብስ እራፊን ቀድዶ ባረጀ ልብስ ላይ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱን ይቀደዋል፤ አዲሱም እራፊ ለአሮጌው አይስማማውም። 37ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ እርሱም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጪ ይሆናል። 38አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል። 39ማንም አሮጌውን የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የሚሻ የለም፤ ‘አሮጌው ይጣፍጣል’ ይላልና።”
अहिले सेलेक्ट गरिएको:
የሉቃስ ወንጌል 5: መቅካእኤ
हाइलाइट
शेयर गर्नुहोस्
कपी गर्नुहोस्
तपाईंका हाइलाइटहरू तपाईंका सबै यन्त्रहरूमा सुरक्षित गर्न चाहनुहुन्छ? साइन अप वा साइन इन गर्नुहोस्

: