ኦሪት ዘፍጥረት 29
29
1ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ። 2በሜዳውም እነሆ ጕድጓድም አየ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በለዩ ተመስገው ነበር ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። 3መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር። 4ያዕቆብም፦ ወንድሞቼ ሆይ እናንት የወዴት ናችሁ? አላቸው። 5እነርሱም፦ እኛ የካራን ነን አሉት የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ እናውቀዋለን አሉት። 6እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። 7እርሱም፦ ቀኑ ገና ቀትር ነው ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩምአቸው አላቸው። 8እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን። 9እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረስች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። 10ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የእጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ ቀረበ ከጕድጓድም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ። 11ያዕቆብም ራሔልን ሳማት ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። 12ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገርችው።
13ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ አቅፎም ሳመው ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው። 14ላባም፦ በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። 15ላባም ያዕቆብን፦ ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ምንዳህ ምንድር ነው? ንገረኝ አለው። 16ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ። 17ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ። 18ያዕቆብም ራሔልን ወደደ እንዲህም አለ፦ ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባር ዓመት እገዛልሃለሁ። 19ላባም፦ ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል ከእኔ ጋር ተቀመጥ አለ። 20ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።
21ያዕቆብም ላባን፦ ወደ እርስዋ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ ቀኔ ተፈጽሞአልና አለው። 22ላባም የዚያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ ሰርግም አደረገ። 23በመሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ለያዕቆብ አገባለት፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ። 24ላባም ለልጁ ለልያ ባሪያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 25በነጋም ጊዜ እንሆ ልያ ሆና ተገኘች፤ ላባንም፦ ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ? አለው። 26ላባም እንዲህም አለ፦ በአገራችን ታላቂቱ ሳለች ታናሺቱን እንስጥ ዘንድ ወግ አይደለም፤ 27ይህችንም ሳምንት ፈጽም ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ። 28ያዕቆብም እንዲህ አደረገ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው። 29ላባም ለልጁ ለራሔል ባርያይቱን ባላን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 30ያዕቆብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔልንም ከልያ ይልቅ ወደዳት ሌላ ሰባት ዓመትም ተገዛለት። 31እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መካን ነበረች። 32ልያም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና። 33ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች፤ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ስማ ይህን ደገመኝ አለች ስምዖን ብላ ጠራችው 34ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። 35ደግሞም ፀነስች ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
Nu geselecteerd:
ኦሪት ዘፍጥረት 29: አማ54
Markering
Deel
Kopiëren
Wil je jouw markerkingen op al je apparaten opslaan? Meld je aan of log in

: