ኦሪት ዘፍጥረት 36

36
1የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፤ እርሱም ኤዶም ነው። 2ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓን የወለዳትን አህሊባማም፥ 3የእስማኤልን ልጅ የነባዮትን እኅት ቤሴሞትን። 4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ 5አህሊባማም የዑስን የዕላምን፥ ቆሬን ወለደች፤ በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው። 6ዔሳውም ሚስቶቹን ወንዶች ልጅቹንና ሴቶች ልጆቹን ቤተሰቡንም ሁሉ ከብቱንም ሁሉ እንስሶቹንም ሁሉ በከንዓንም አገር ያገኘውን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ፊት ወደ ሌላ አገር ሄደ። 7ከብታቸው ስለ በዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልታሉም በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም። 8ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።
9በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። 10የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል። 11የኤልፋዝም ልጆች እንዚህ ናቸው፤ ቴማን አማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ። 12ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ የጭን ገረስ ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው። 13የራጉኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። 14የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው ለዔሳውም የዑስን፥ የዕላማን፥ ቆሬን ወለደች።
15የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው ለዔሳው የበኵር ለኤፋዝ ልጆች ቴማን አለቃ እማር አለቃ ስፎ አለቃ ቄኔዝ አለቃ 16ኮሬ አለቃ ጎቶም አለቃ አማሌቅ አለቃ በኤዶም ምድር የኤልፋእ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። 17የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች እነዚህ ናቸው ናሖት አለቃ ዛራ አለቃ ሣማ አለቃ ሚዛህ እለልቃ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። 18የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው የዑስ አለቃ የዕላማ አለቃ ቆሬ አለቃ የዔሳው ሚስት የዓን ልጅ የአህሊባማ አለቆአ እነዚህ ናቸው። 19የዔሳው ልጆችን አለቆቻቸስ እነዚህ ናቸው እርሱም ኤዶም ነው።
20በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው ሎጣን፥ ሦባል 21ፅብዖም፥ ዓን፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን እንዚህ በኤዶም ምድር የሖሪው የሴይር ልጆች አለቆች ናቸው። 22የሎጣን፥ እኅት ሖሮ ሄማም ናቸው የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ናት 23የሦባል ልጆችም እንዚህ ናቸው ዓልዋን፥ ማኔሐት ዔባል ስፎ አውናም የፅብዓን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ 24አያዓና ይህም ዓና በምድረ በዳ የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ ፍልውኆችን ያገኘ ነው። 25የዓና ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዲሶን፥ አህሊባማም የዓን ሴት ልጅ። 26የዲሶንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሔምዳን ኤስባን፥ ይትራን ክራን። 27የኤጽር ልጆችም እነዚህ ናቸው ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን 28የዲሳን ልጆችም እነዚህ ናቸው ዑፅ አራን። 29የሖሪ አለቆች እነዚህ ናቸው ሎጣን አለቃ ሦባል አለቃ ፅብዖን አለቃ፥ 30ዓና አለቃ፥ ዲሶን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ ዲሳን አለቆቹ፤ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው።
31በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። 32በኤዶምም የቢዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት። 33ባላቅም ሞተ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ ኢዮባብም ሞተ 34በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ 35ሑሳምም ሞተ በስፍራውም የምድያምን ስዎች በሞዓብ ሜዳ የመታ የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ። 36ሃዳድም ሞተ በስፍራውም የመሥሬቃው ሠምላ ነገሠ። 37ሠምላም ሞተ በስፍራውም በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርሆቦት ሳኦል ነገሠ። 38ሳኦልም ሞተ በስፍራውም የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ። 39የዓክቦር ልጅ በኣልሐናንም ሞተ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ነው ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባላለች።
40የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፤ 41አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ ፊኖን አለቃ 42ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ 43መግዲኤል አለቃ ዒራም አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ይህ ዔሳው ነው።

Markering

Deel

Kopiëren

None

Wil je jouw markerkingen op al je apparaten opslaan? Meld je aan of log in