ኦሪት ዘፍጥረት 3
3
የአዳም ኃጢአት እና ውድቀት
1 #
ጥበ. 2፥24፤ ራእ. 12፥9፤ 20፥2። ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ#3፥1 እዚህ ላይ እባቡ አሳሳች ተደርጎ ሲቀርብ የእግዚአብሔርና የሰው ዘር ጠላት በመሆን፥ በጥበብ መጽሐፍ (በተለይም ኢዮብ 1፥6)፥ በአዲስ ኪዳን እና በክርስትና ትውፊት፥ ተቃዋሚውን ወይም ዲያቢሎስን የሚያመለክት ነው። ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት። 2ሴቲቱም ለእባቡ አለችው፦ “በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ ልንበላ እንችላለን፤ 3ነገር ግን እግዚአብሔር ‘በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፥ አትንኩትም።’” ብሏል። 4እባብ ግን ለሴቲቱ አላት፦ “በፍጹም አትሞቱም፥ 5ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዐይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ፥ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።”
6ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ጥበብ ለማግኘትም የሚመኙት እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም በላ። 7የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፥ ስለዚህ የበለስን ቅጠሎች ሰፍተው በማገልደም እርቃናቸውን ሸፈኑ። 8ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
9ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ጠርቶ፦ “ወዴት ነህ?” አለው። 10እርሱም፥ “በገነት ድምጽህን ሰማሁ፥ ዕራቁቴንም ስለ ሆንኩ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።” አለ። 11እግዚእብሔርም፦ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ ከእርሱ በላህን?” አለው። 12አዳምም፦ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኽኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። 13#2ቆሮ. 11፥3፤ 1ጢሞ. 2፥14።ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች። 14ጌታ እግዚአብሔርም እባቡን አለው፦
“ይህን በማድረግህ፥
ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤
በሆድህም ትሄዳለህ፥
በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።
15 #
ራእ. 12፥17። “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥
“በዘርህና በዘርዋም መካከል
ጠላትነትን አደርጋለሁ፥
እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥
አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
16ለሴቲቱም አላት፥
“በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥
በጭንቅ ትወልጃለሽ፥
ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥
እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”
17 #
ዕብ. 6፥8። አዳምንም አለው፦
“የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥
እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም ከእርሱ በልተሃልና
ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፥
በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ ትበላለህ፤
18“እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፥
የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።”
19“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ
በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥
አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”
20አዳምም ለሚስቱ “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣ፤ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና። 21ጌታ እግዚአብሔርም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።
22 #
ራእ. 22፥14። ከዚያም ጌታ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፥ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘለዓለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር”፥ አለ። 23ስለዚህ፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ፥ ጌታ እግዚአብሔር ከዔድን ገነት አስወጣው። 24አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።
Aktualisht i përzgjedhur:
ኦሪት ዘፍጥረት 3: መቅካእኤ
Thekso
Ndaje
Copy
A doni që theksimet tuaja të jenë të ruajtura në të gjitha pajisjet që keni? Regjistrohu ose hyr

: